ቅዱሳት መጻህፍት
አልማ ፪


ምዕራፍ ፪

አምሊኪ ንጉስ ለመሆን ፈለገ እናም በህዝቡ ድምፅ ተቀባይነት አላገኘም—ተከታዮቹ ንጉስ አደረጉት—አምሊኪውያን ከኔፋውያን ጋር ተዋጉ እናም ተሸነፉ—ላማናውያንና አምሊኪውያን ኃይላቸውን በአንድ ላይ አደረጉ፣ እናም ተሸነፉ—አልማ አምሊኪን ገደለው። ከ፹፯ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንዲህ ሆነ በአምስተኛው የንግስና ዓመታቸው መጀመሪያ በህዝቡ መካከል ጠብ ተጀመረ፤ እጅግ አጭበርባሪ፣ አዎን ለዓለም ጥበብ ብልህ ሰው የሆነ፣ በህግ መሰረት በተገደለው ጌዴዎንን በገደለው ሰው ሥርዓት መሠረት የነበረው አምሊኪ ተብሎ የሚጠራው ሰው ነበር።

አሁን አምሊኪ በብልሀቱ ብዙ ሰዎች እንዲከተሉት አደረገ፣ ብዙዎች እንኳን ሆነው እጅግ ኃያል መሆን ጀመሩ፤ እናም አምሊኪ በህዝቡ ላይ ንጉስ እንዲሆን ጥረት ማድረግ ጀመሩ።

እንግዲህ ይህ ለቤተክርስቲያኗ ሰዎች፣ እናም ደግሞ በአምሊኪ ጉትጎታ ላልተወሰዱት ሁሉ አስጊ ነበር፤ በህጋቸው መሰረት እንደዚህ ያሉ ነገሮች በህዝቡ ድምፅ መመስረት ያለባቸው እንደሚሆኑ ያውቃሉና።

ስለዚህ አምሊኪ የህዝቡን ድምፅ ማግኘት የሚችል ከሆነ፣ እርሱ ክፉ ሰው ስለነበረ፣ በቤተክርስቲያን ያላቸውን መብትና እድል ይከለክላቸዋል፤ ዓላማው የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ለማጥፋት ነበርና።

እናም እንዲህ ሆነ እያንዳንዱ ሰው እንደአስተሳሰቡ፣ በአምሊኪ ይሁን ወይም እርሱን ለመቃወም፣ በተለያየ አካል በመሆን፣ አንዱ ከሌላውጋር ታላቅ ፀብና አስገራሚ ጥል በማድረግ በምድሪቱ ላይ ሁሉ ተሰበሰቡ።

እናም ጉዳዩን በተመለከተ ድምፅ ለመስጠት እራሳቸውን በአንድ ላይ ሰበሰቡ፣ እናም በዳኛዎች ፊት ቀርበው ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ የህዝቡ ድምፅ በአምሊኪ ላይ ሆነ፣ እርሱም በህዝቡ ላይ ንጉስ አልተደረገም ነበር።

እንግዲህ ይህ ከእርሱ ተቃራኒ ለሆኑት ታላቅ ደስታን በልባቸው እንዲሆን ያደርጋል፤ ነገር ግን አምሊኪ የእርሱ ደጋፊዎች የሆኑት ደጋፊዎች ያልሆኑት ላይ እንዲያውኩ አደረገ።

እናም እንዲህ ሆነ እራሳቸውን በአንድነት ሰበሰቡ፣ እናም አምሊኪን ንጉስ አድርገው ቀቡት።

እናም አምሊኪ በእነርሱ ላይ ንጉስ በተደረገ ጊዜ እነርሱ በወንድሞቻቸው ላይ የጦር መሳሪያዎቻቸውን እንዲያነሱ አዘዘ፤ እናም ይህንን ያደረገው በእርሱ ስር ያደርጋቸው ዘንድ ነው።

፲፩ እንግዲህ የአምሊኪ ሰዎች አምሊኪውያን ተብለው በአምሊኪ ስም በመጠራት ይታወቃሉ፤ እናም ቀሪዎቹ ኔፋውያን፣ ወይም የእግዚአብሔር ሰዎች ተብለው ይጠራሉ።

፲፪ ስለዚህ የኔፋውያን ህዝብ የአምሊኪውያንን ዓላማ ያውቁ ነበር፣ እናም ስለዚህ ከእነርሱ ጋር ለመገናኘት ተዘጋጁ፤ አዎን በጎራዴም፣ በሻሙላም፣ በሰይፍ፣ በቀስትም፣ በድንጋይና በወንጭፍ፣ እናም በሁሉም ዓይነት የጦር መሳሪያዎች ከሁሉም ዓይነት እራሳቸውን አስታጠቁ።

፲፫ እናም በሚመጡበት ጊዜ አምሊኪውያንን ለመገናኘት እንደዚህ ተዘጋጅተው ነበር። እናም እንደብዛታቸው አምበሎችና፣ ከፍተኛ የቡድን አለቆች፣ እንዲሁም የበላይ ሻምበሎች ተሹመው ነበር።

፲፬ እናም እንዲህ ሆነ አምሊኪ ከሁሉም ዓይነት የጦር መሳሪያዎች ህዝቡን አስታጥቆ ነበር፤ እናም ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር ለማዋጋት እንዲመሩአቸው ገዢዎችንና መሪዎችን በህዝቡ ላይ ሾመ።

፲፭ እናም እንዲህ ሆነ አምሊካውያኑ ወደ ዛራሄምላ ምድር በሚፈሰው በሲዶም ወንዝ በስተምስራቅ በኩል ባለው በአምኒሁ ኮረብታ ላይ ሆኑ፣ እናም ከኔፋውያን ጋር ጦርነት ጀመሩ።

፲፮ እንግዲህ አልማ የኔፋውያን ዋና ዳኛ እናም የህዝቡ አስተዳዳሪ በመሆኑ፣ ከህዝቡ ጋር አዎን ከሻምበሎቹ ጋር፣ እናም ከበላይ ሻምበሎቹ ጋር አዎን ከወታደሮቹ ፊት በመሆን ከአምሊኪውያን ጋር ለመዋጋት ሄደ።

፲፯ እናም በሲዶም በስተምስራቅ ኮረብታ ላይ አምሊኪውያንን መግደል ጀመሩ። እናም አምሊኪውያን በታላቅ ብርታት በርካታ ኔፋውያን ከአምሊኪውያን ፊት እስኪወድቁ ከኔፋውያን ጋር ተዋጉ።

፲፰ ይሁን እንጂ ጌታ በታላቅ ግድያ አምሊኪውያን እንዲገደሉ የኔፋውያንን ክንድ አበረታ፤ እነርሱም ከፊታቸው መሸሽ ጀመሩ።

፲፱ እናም እንዲህ ሆነ ኔፋውያን በዚያን ቀን ሁሉ አምሊኪውያንን ተከተሉ፣ እናም አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሠላሣ ሁለት አምሊኪውያንን ነፍስ እስኪገደሉ ድረስ በታላቅ ግድያ ገደሉአቸው፤ እናም ስድስት ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ሁለት የኔፋውያን ነፍስ ጠፍተው ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ አልማ ምንም እንኳን አምሊኪውያንን ለማሳደድ በማይችልበት ጊዜ፣ በኔሆር እጅ በጎራዴ በተገደለው በጌዲዮን ስም በተሠየመ ሸለቆው፣ በጌዴዎን ሸለቆ ህዝቡ ድንኳናቸውን እንዲተክሉ አደረገ፤ እናም በዚህ ሸለቆ ኔፋውያን ለምሽት ድንኳናቸውን ተክለው ነበር።

፳፩ እናም አልማ የአምሊኪውያንን ዕቅድና ሴራ ያውቅ ዘንድ፣ በዚያም እራሱን ከእነርሱ ይጠብቅ ዘንድ፣ ህዝቡንም ከጥፋት ይጠብቅ ዘንድ ቅሪቶቻቸውን ለመከታተል ሰላዮችን ላከ።

፳፪ አሁን የአምሊኪውያንን የጦር ሰፈር እንዲመለከቱ የላካቸው ዜራምና፣ አምኖርም፣ ማንቲና ሊምኸር ተብለው ይጠራሉ፤ እነዚህ የአምሊኪውያንን የጦር ሰፈር እንዲመለከቱ ከወንድ ሰዎቻቸው ጋር የሄዱት ናቸው።

፳፫ እናም እንዲህ ሆነ በማግስቱ ወደ ኔፋውያን የጦር ሰፈር በችኮላ ተመለሱ፣ በኃይል በመገረም እናም በታላቅ ፍርሃት እንዲህ አሉ፥

፳፬ እነሆ የአምሊኪውያንን የጦር ሰፈር ተከተልን፣ በሚኖን ምድር ከዛራሄምላ ምድር ከፍ ብሎ ወደ ኔፊ ምድር በሚወስደው በርካታ የላማናውያን ሰራዊቶችን ተመለከትን፤ እናም እነሆ አምሊኪውያን እነርሱን ተገናኙአቸው፤

፳፭ እናም በምድሪቱ በወንድሞቻችን ላይ ናቸው፤ እናም ከመንጋዎቻቸውና፣ ከሚስቶቻቸው፣ እናም ከልጆቻቸው ጋር ወደ እኛ ከተማ እየሸሹ ናቸው፤ እናም እኛ ካልፈጠንን በስተቀር ከተማችንን ይወስዱብናል፣ እናም አባቶቻችንና ሚስቶቻችን እንዲሁም ልጆቻችን ይገደላሉ።

፳፮ እናም እንዲህ ሆነ የኔፊ ህዝብ ድንኳናቸውን ወሰዱ፣ እናም ከጌዴዎን ሸለቆ ወጥተው የዛራሄምላ ከተማ ወደ ነበረው ወደ ራሳቸው ከተማ ሄዱ።

፳፯ እናም እነሆ፣ የሲዶምን ወንዝ ባቋረጡበት ጊዜ እንደ ባህር አሸዋ ቁጥራቸው የበዛ የሚመስሉት ላማናውያንና አምሊኪውያን ሊያጠፉአቸው መጡ።

፳፰ ይሁን እንጂ ኔፋውያን በጌታ ክንድ ብርታትን በማግኘታቸው እርሱ ከጠላቶቻቸው እጅ ያስለቅቃቸው ዘንድ በኃይል ፀለዩ፤ ስለዚህ ጌታ ጩኸታቸውን ሰማና አበረታቸው፣ እናም ላማናውያንና አምሊኪውያን በፊታቸው ወደቁ።

፳፱ እናም እንዲህ ሆነ አልማ ከአምሊኪ ጋር በጎራዴ ፊት ለፊት ተፋለመ፣ እናም እርስ በእርሳቸው በኃይል ተጣሉ።

እናም እንዲህ ሆነ አልማ የእግዚአብሔር ሰው በመሆኑ፣ በእምነትም የተነሳሳ በመሆኑ እንዲህ በማለት ጮኸ፥ አቤቱ ጌታ ምህረትህ በእኔ ላይ ይሁን እናም ነፍሴን አትርፍ፣ እኔም ይህንን ህዝብ አድነውና እጠብቀው ዘንድ በእጅህ መሳሪያ እሆን ዘንድ።

፴፩ አሁን አልማ እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ ከአምሊኪ ጋር እንደገና ታገለ፤ አምሊኪን በጎራዴ እስኪገድለውም በርትቶ ነበር።

፴፪ እናም ደግሞ እርሱ ከላማናውያን ንጉስ ጋር ታግሎ ነበር፤ ነገር ግን የላማናውያን ንጉስ ከአልማ ፊት ሸሸ እናም ከአልማ ጋር እንዲታገሉ ጠባቂዎቹን ላከ።

፴፫ ነገር ግን አልማ ከጠባቂዎቹ ጋር፣ ከላማናውያን ንጉስ ጠባቂዎች ጋር እነርሱን በመግደል እስኪመልሳቸው ድረስ ተዋጋ።

፴፬ እናም የተገደሉትን የላማናውያንን ሬሳ በሲዶም ወንዝ በመጣል፣ ህዝቡም ከላማናውያንና ከአምሊኪውያን ጋር በሲዶም ወንዝ በስተምዕራብ በኩል በማቋረጥ እንዲዋጉ ቦታ ይኖራቸው ዘንድ ቦታውን በሌላ አነጋገር ከሲዶም ወንዝ በስተምዕራብ በኩል ያለውን ዳርቻ እንደዚህ አጠራ።

፴፭ እናም እንዲህ ሆነ ሁሉም የሲዶምን ወንዝ ባቋረጡ ጊዜ፣ ምንም እንኳን እጅግ ብዙ ሆነው ለመቁጠር የማይቻል ቢሆኑም ላማናውያንና አምሊኪውያን ከፊታቸው መሸሽ ጀመሩ።

፴፮ እናም ከምድሪቱ ዳርቻ በስተምዕራብና በስተሰሜን በኩል ወዳለው ምድረበዳ ከኔፋውያን ፊት ሸሹ፤ እናም ኔፋውያን በኃይላቸው አሳደዱአቸውና ገደሉአቸው።

፴፯ አዎን፣ በየአቅጣጫው ተገናኙአቸው፤ እናም በምዕራብና በሰሜን በኩል እስኪበተኑ ድረስ በስተሰሜን በኩል ሔርማውንትስ ከሚባለው ስፍራ በምድረበዳው እስከሚደርሱ ድረስ አባረሩአቸው እናም ገደሉአቸው፤ እና ይህም በዱርና በስግብግብ አውሬዎች የተወረረው ምድረበዳ ክፍል ነበር።

፴፰ እናም እንዲህ ሆነ ብዙዎች በቁስላቸው በምድረበዳው ሞቱና፣ በአውሬዎቹና ደግሞ በጥንብ አንሳዎች ተበሉ፤ እናም አጥንታቸው በምድር ላይ ተቆልሎ ተገኘ።