ምዕራፍ ፲፮
ላማናውያን የአሞኒሀን ህዝብ አጠፉ—ዞራም ኔፋውያን ላማናውያንን ድል እንዲያደርጉ መራቸው—አልማና አሙሌቅ እናም ሌሎች ብዙዎች ቃልን ሰበኩ—ከትንሣኤው በኋላም ክርስቶስ ለኔፋውያን እንደሚገለፅ አስተማሩአቸው። ከ፹፩–፸፯ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም እንዲህ ሆነ በኔፋውያን ላይ በመሣፍንቱ አስራ አንደኛ ዓመት የንግስ ዘመን፣ በሁለተኛው ወር አስራ አምስተኛ ቀን፣ በዛራሔምላ ታላቅ ሰላም ሆነ፣ ጦርነትም ይሁን ፀብ ለተወሰኑ ዓመታት፣ እንዲሁም እስከ አስራ አንደኛው ዓመት በሁለተኛው ወር እስከ አምስተኛው ቀን ድረስ እንኳን አልነበረም፣ በምድሪቱ ላይ ሁሉ የጦርነት ጩኸትተሰማ።
፪ እነሆም፣ የላማናውያን ወታደሮች በምድረበዳው በኩል በምድሪቱ ዳርቻ ወደ ሀአሞኒሀ ከተማ ሄዱ፣ እናም ህዝቡን መግደል ከተማዋንም ማጥፋት ጀመሩ።
፫ እናም አሁን እንዲህ ሆነ፣ ኔፋውያን እነርሱን ከምድሪቱ ለማስወጣት በቂ ወታደሮችን ከመመልመላቸው በፊት፣ በአሞኒሀ ከተማ ያሉትንና ደግሞ ጥቂት በኖህ ዳርቻ ዙሪያ ያሉትን ሰዎች ሀአጠፉአቸው፣ እናም ሌሎችን በምርኮኛነት ወደ ምድረበዳው ወሰዱአቸው።
፬ አሁን እንዲህ ሆነ ኔፋውያን ወደ ምድረበዳው በምርኮ የተወሰዱትን ለማግኘት ፈለጉ።
፭ ስለዚህ፣ በኔፋውያን ወታደሮች ላይ ዋና ሻምበል ሆኖ የተሾመው (ዞራም ተብሎ የሚጠራው፣ እናም ሌሂና አሃ የተባሉ ሁለት ወንድ ልጆች ያሉት)—አሁን ዞራምና ሁለቱ ወንድ ልጆቹ አልማ በቤተክርስቲያኗ ላይ ሊቀ ካህን መሆኑን በማወቃቸው፣ እናም የትንቢት መንፈስ እንዳለው በመስማታቸው፤ ስለዚህ ጌታ በላማናውያን በምርኮ የተወሰዱባቸውን ወንድሞቻቸውን ለመፈለግ ወደ ምድረበዳው የት መሄድ እንዳለባቸው ለማወቅ ወደ እርሱ ሄዱ።
፮ እናም እንዲህ ሆነ አልማ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ጌታን ሀጠየቀ። እናም አልማ ተመለሰና እንዲህ አላቸው፥ እነሆ፣ ላማናውያን በምድረበዳው በስተደቡብ በማንቲ ምድር ዳርቻ ራቅ ብሎ የሲዶምን ወንዝ ያቋርጣሉ። እናም እነሆ በሲዶም ወንዝ በስተምስራቅ ከእነርሱ ጋር ትገናኛላችሁ፣ እናም በላማናውያን በምርኮ የተወሰዱትን ወንድሞቻችሁን ጌታ ለእናንተ ይሰጣችኋል።
፯ እናም እንዲህ ሆነ ዞራምና ወንድ ልጆቹ ከወታደሮቻቸው ጋር የሲዶምን ወንዝ አቋረጡ፣ እናም በማንቲ ዳርቻ በምድረበዳው በስተደቡብ በኩል፣ በሲዶም ወንዝ በስተምስራቅ ዘመቱ።
፰ እናም በላማናውያን ወታደሮች ላይ መጡባቸው፣ እናም ላማናውያን ተበታተኑና ወደ ምድረበዳው ሸሹ፤ እናም በላማናውያን የተማረኩ ወንድሞቻቸውን ወሰዱና፣ በምርኮ ከተወሰዱት ውስጥ አንድም ነፍስ አልሞተባቸውም ነበር። እናም በወንድሞቻቸው ምድራቸውን ሊወርሱ ዘንድ ተወሰዱ።
፱ እናም የመሣፍንቱ አስራ አንደኛ ዓመት እንደዚህ ተፈፀመ፤ ላማናውያን ከምድሪቱ ወጡና፣ የአሞኒሀውያን ህዝቦችም ሀጠፉ፤ አዎን፣ በህይወት የነበሩ አሞናውያን ሁሉ፣ እናም ደግሞ በታላቅነቷ የተነሳ እግዚአብሔር ሊያጠፋት አይቻለውም የተባለላት ታላቋ ከተማቸውም ለጠፋች።
፲ ነገር ግን እነሆ፣ ሀበአንድ ቀን ባዶ ሆነች፤ እናም ሬሳዎች በምድረበዳው ውሾችና በዱር አውሬዎች ተቆራረጡ።
፲፩ ይሁን እንጂ፣ ከብዙ ቀናት በኋላ ሬሳዎቻቸው በምድሪቱ ላይ ተቆለሉና፣ ጥልቅ ባልሆነ ሽፋን ተሸፈኑ። እናም እንዲሁም ሽታው በማየሉ ህዝቡ ለብዙ ዘመናት የአሞኒያህን ምድር ለመያዝ አልገቡም ነበር። ይህም የኔሆራውያን መውደም ተብሎ ይጠራ ነበር፤ የተገደሉት ሀየኔሆርን ኃይማኖት ተከታዮች ነበሩና፣ እናም ምድራቸው ባዶ ሆና ቀረች።
፲፪ እናም መሣፍንቱ በኔፊ ህዝቦች ላይ እስከሚነግሱበት አስራ አራተኛ ዓመት ድረስ ላማናውያን በኔፊ ህዝቦች ላይ ለጦርነት አልመጡም። እናም ለሶስት ዓመታት የኔፊ ህዝብ በምድሪቱ ላይ የማያቋርጥ ሰላምን አገኙ።
፲፫ እናም አልማና አሙሌቅ ለህዝቡ ስለንስሃ ለመስበክ ሀበቤተመቅደሶቻቸው፣ እናም ደግሞ በቅዱስ ሥፍራዎቻቸው፣ እናም ደግሞ በአይሁድ ስርዓት በተገነቡት ለምኩራቦቻቸው ሄዱ።
፲፬ እናም ቃላቸውን ላዳመጡአቸው ሁሉ፣ ሀያለማዳላት ሳያቋርጡ የእግዚአብሔርን ቃል አካፈሉአቸው።
፲፭ እናም አልማና አሙሌቅ፣ ደግሞም ከዚህ የበለጡ ለስራው የተመረጡ ብዙዎች በምድሪቱ ላይ ቃሉን ለመስበክ ሄዱ። እናም ቤተክርስቲያኗ በምድሪቱ ላይ በዙሪያው በኔፋውያን ሁሉ መካከል ተቋቋመች።
፲፮ እናም በእነርሱ መካከል ምንም ዓይነት ሀእኩል ያልሆነ አልነበረም፤ ጌታ የሰው ልጆችን አዕምሮ ለማዘጋጀት እንዲሁም በመምጫው ጊዜ በእነርሱ መካከል የሚሰበከውን ቃል ለመቀበል ለልባቸውን እንዲያዘጋጁ በምድሪቱ ላይ ሁሉ መንፈሱን አፈሰሰ—
፲፯ በቃሉ ላይ ልባቸውን እንዳያጠጥሩ፣ የማያምኑ እንዳይሆኑ፣ እናም ወደ ጥፋት እንዳይሄዱ፣ ነገር ግን ቃሉን በደስታ ይቀበሉት ዘንድ እናም ሀቅርንጫፉ ወደ እውነተኛው ለወይን እንዲዳቀሉ ዘንድ፣ እነርሱም ወደ ጌታ አምላካቸው ሐእረፍት ይገቡ ዘንድ ነው።
፲፰ አሁን ውሸቶችንም፣ ሀማታለልንም፣ ለቅናትንም፣ ጠብንም፣ ተንኮልንም፣ ስድብንም፣ ስርቆትንም፣ ዝርፊያንም፣ መቀናትንም፣ ግድያንም፣ ዝሙት መፈፀምንም፣ እናም ሁሉም አይነት ምንዝርናን እንዲያስወግዱ ከህዝቡ መካከል የሰበኩት እነዚያ ሐካህናት፣ እነዚህ ነገሮች እንዳይሆኑ ጮሁ—
፲፱ በቅርብ የሚመጡትን ነገሮች ካህናቱ በማወጅ፤ አዎን፣ ሀየእግዚአብሔርን ልጅ መምጣት፣ ስቃዩንና ሞቱን፣ እናም ደግሞ ከሙታን መነሳቱን በማወጅ ጮሁ።
፳ እናም ብዙዎች የእግዚአብሔር ልጅ የሚመጣበትን ስፍራ በተመለከተ ጠየቁ፤ እርሱም ሀከትንሣኤው በኋላ ለእንደሚገለጥላቸው ተምረው ነበር፤ እናም ህዝቡ ይህንን ያዳመጠው በታላቅ ሀሴትና ደስታ ነበር።
፳፩ እናም አሁን ቤተክርስቲያኗ በምድሪቱ ላይ ከተመሰረተች በኋላ—በዲያብሎስ ላይ ሀድል ካገኘች፣ እናም በንፅህና በምድሪቱ ላይ የጌታ ቃል አንድ ላይ ከተሰበከ በኋላ፣ እናም ጌታ በህዝቡ ላይ በረከትን አፈሰሰ—በኔፊ ህዝብ ላይ አስራ አራተኛው የመሣፍንት የንግስ ዘመን በዚሁ ተፈፀመ።