ቅዱሳት መጻህፍት
አልማ ፲፫


ምዕራፍ ፲፫

ሰዎች በታላቁ እምነታቸውና በመልካም ስራዎቻቸው ሊቀ ካህን ተብለው ይጠራሉ—ትዕዛዛቱን ያስተምሩ—በፅድቅ ይቀደሳሉ እናም ወደጌታ እረፍት ይገባሉ—መልከ ጼዴቅ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ነበር—መላዕክት የምስራች ወሬውን በምድሪቱ ያውጃሉ—የክርስቶስን በእርግጥ መምጣቱን ያውጃሉ። በ፹፪ ም.ዓ. ገደማ።

እናም በድጋሚ፣ ወንድሞቼ፣ ጌታ እግዚአብሔር እነዚህን ትዕዛዛት ለልጆቹ ወደሰጠበት ጊዜ አዕምሮአችሁን እጠቁማለሁ፤ እናም ጌታ እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ለህዝብ እንዲያስተምሩ የልጁ ቅዱስ ሥርዓት መሰረት በሆነው በቅዱስ ሥርዓቱ ካህናትን መሾሙን እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ።

እናም ካህናቱ የተሾሙት በልጁ ሥርዓት መሠረት ነበር፣ በስርዓቱም ህዝቡ ወልድን ለቤዛቸው በምን ሁኔታ መመልከት እንዳለባቸው ያውቁ ዘንድ ነው።

እናም የተሾሙበት ሥርዓት በዚህ ሁኔታ ነበር—እናም ከዓለም መፈጠር ጀምሮ በእግዚአብሔር በቀደመው እውቀት መሰረት በእምነታቸውና በመልካም ስራዎቻቸው ተጠርተዋልተዘጋጅተዋልም፤ በመጀመሪያ ደረጃ መጥፎና ጥሩውን እንዲመርጡ ተትተዋል፤ ስለዚህ መልካሙን በመምረጣቸውና ታላቅ እምነትን በመለማመዳቸው በቅዱሱ አጠራር፣ አዎን፣ ለእንደእነዚህ አይነት ሰዎች በቤዛነት ዝግጅት ጋር፣ እናም መሰረት፣ በተዘጋጀው ቅዱስ ጥሪ ተጠርተዋል

እናም በእምነታቸው የተነሳ ለዚህ ቅዱሱ ጥሪ እንደዚህም ተጠርተዋል፣ ይህ ሆኖ ሳለ፣ ሌሎች በልባቸው ጠጣርነትና በአዕምሮአቸው መታወር የእግዚአብሔርን መንፈስ አይቀበሉ፣ በሌላ መልኩ፣ በዚህ ባይሆን ኖሮ እንደወንድሞቻቸው ታላቅ መብት ይኖራቸው ነበር።

በአጠቃላይ በመጀመሪያ ደረጃ እነርሱ ከወንድሞቻቸው ጋር አንድ ዓይነት አቋም ነበራቸው፣ ይህ ቅዱሱ ጥሪም ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ልባቸውን ላላጠጠሩት ተዘጋጅቷል፣ የተዘጋጀውም በአንድያ ልጁ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት በኩል እና ውስጥ ነበር—

እናም በቅዱሱ ጥሪው እንዲህ በመጠራትና፣ ወደ እረፍቱም ይገቡ ዘንድ ለሰው ልጆች ትዕዛዛቱን ለማስተማር በእግዚአብሔር ቅዱሱ ስርዓት መሠረት ወደ ታላቁ ክህነት ተሹመዋል—

ይህም ታላቁ ክህነት ከአለም መፈጠር ጀምሮ ከነበረው ከወልድ ሥርዓት መሰረት ነው፤ ወይም በሌላ አነጋገር፣ መጀመሪያም ቀናት ሆነ ፍፃሜ አመታት የሌለው፤ ለሁሉም ነገር በቀደመው እውቀቱ መሰረት ከዘለዓለም እስከዘለዓለም የተዘጋጀ ነው—

አሁን በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ተሹመዋል—በቅዱሱ ጥሪም ተጠርተውና፣ በቅዱሱ ስርዓት ተሹመው፣ ጥሪውና፣ ሹመቱ፣ እና ታላቁ ክህነት መጀመሪያና መጨረሻ የሌለውን የቅዱሱን ስርዓት ታላቅ ክህነት ተቀብለዋል—

መጀመሪያ ቀናት ሆነ መጨረሻ አመታት በሌለው፣ በፀጋ፣ ፍትህና እውነት በተሞላው በአብ አንድያ ልጅ፣ እንደ ወልድ ስርዓት መሠረት ለዘለአለም ሊቀ ካህናት እንደዚህ ሆኑ። እናም እንደዚህ ነው። አሜን።

እንግዲህ፣ ስለቅዱሱ ስርዓትም ሆነ ስለዚህ ታላቁ ክህነት በተመለከተ በተናገርኩ ጊዜ፣ ብዙዎች የተሾሙና የአምላክ ሊቀ ካህን የሆኑ ነበሩ፤ እናም ይህም በታላቁ እምነታቸውና ንስሃ በመግባታቸው፣ እናም በእግዚአብሔር ፊት ባላቸው ብፁዕነት ንስሃ ለመግባትና ከመጥፋትም ፅድቅን ለመስራት በመምረጣቸው ምክንያት ነው፤

፲፩ ስለዚህ በዚህ ቅዱስ ስርዓት ተጠርተው ነበር፣ ተቀድሰውም ነበር፣ እናም በበጉ ደም ልብሳቸው እስከሚነጣ ታጥበው ነበር።

፲፪ እንግዲህ እነርሱ በቅዱስ መንፈስ ከተቀደሱ በኋላ፣ ልብሳቸው ከነጣ፣ በአምላክ ፊት ንፁህና እንከን የለሽ ከሆኑ፣ ኃጢያትን ከመጥላት በቀር ሊመለከቱትም አልቻሉም፣ እናም ንፁህ የሆኑና ወደጌታ አምላካቸው እረፍት የገቡ ብዙዎች፣ እጅግ ብዙዎች፣ ነበሩ።

፲፫ እናም አሁን፣ ወንድሞቼ፣ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ትሁት እንድታደርጉ፣ እናም ለንስሃም ብቁ የሆነ ፍሬን እንድታመጡ፣ እናንተም በእረፍቱ ትገቡ ዘንድ እፈልጋለሁ።

፲፬ አዎን፣ እኔ በተናገርኩት ተመሳስይ ሥርዓት መሠረት ሊቀ ካህን የነበረው፤ ታላቁ ክህነትን ለዘለአለም እንደተቀበለው መልከ ፄዴቅ ጊዜ እንደነበሩት ሰዎች ራሳችሁን ትሁት አድርጉ።

፲፭ እናም ለዚህ መልከ ፄዴቅ ነበር አብርሃም አስራት የከፈለው፣ አዎን፣ አባታችን አብርሃም ከነበረው ሀብት እንኳን አንድ አስረኛውን አስራት ከፍሏል።

፲፮ አሁን ይህ የሥርዓቱም ሁኔታ ሆኖ ወይንም ይህ የእርሱ ሥርዓት ሆኖ፣ በዚህ ህዝብ ወደ እግዚአብሔር ልጅ ይመለከቱ ዘንድ እነዚህ ስርዓቶች በዚህ ሁኔታ ነበር የተሰጡት፣ እና ይህም ለኃጢአታቸው ሥርየትም ወደፊት ወደእርሱ ይመለከቱት ዘንድ፣ ወደጌታም ዕረፍት ይገቡበት ዘንድ ነው።

፲፯ እንግዲህ ይህ መልከ ፄዴቅ በሳሌም ምድር ንጉስ ነበር፣ እናም ህዝቡም በክፋትና በእርኩሰታቸው የጠነከሩ ነበሩ፤ አዎን፣ ሁሉም የተሳሳቱ ነበሩ፤ በሁሉም ዓይነት ክፋትም ተሞልተው ነበር።

፲፰ ነገር ግን መልከ ፄዴቅ ታላቅ እምነትን ተለማመደ፣ የታላቅ ክህነት ሀላፊነትን በእግዚአብሔር ቅዱሱ ስርዓት መሰረት በመቀበል ለህዝቡ ንስሃን ሰበከ። እናም እነሆ፣ እነርሱ ንስሃ ገቡ፤ በዘመኑም መልከ ጼዴቅ ሰላምን በምድር ውስጥ መሰረተ፤ ስለዚህ የሳሌም ንጉስ በመሆኑ የሰላም አለቃ ተብሎ ተጠርቷል፤ እናም በአባቱም በታች ነገሰ።

፲፱ አሁን፣ ከፊቱ ብዙዎች ነበሩ፣ እናም ደግሞ ከእርሱ በኋላ ደግሞ ብዙዎች ነበሩ፣ ነገር ግን ማንም ታላቅ አልነበረም፤ ስለዚህ፣ በይበልጥ ስለእርሱ በልዩ ጠቅሰዋል።

አሁን ይህን ጉዳይ እንደገና መናገር አያስፈልገኝም፣ የተናገርኩት ይበቃል። እነሆ፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ከፊታችሁ ይገኛሉ፤ የምታጣምሙት ከሆነ ለጥፋታችሁ ይሆናል።

፳፩ እናም አሁን እንዲህ ሆነ አልማ እነዚህን ቃላት ለእነርሱ በተናገረ ጊዜ፣ እጁን ዘርግቶ በኃይል እንዲህ በማለት ይጮህ ነበር፥ አሁን የንስሃ ጊዜ ነው፣ የደህንነት ቀን ቀርባለችና፤

፳፪ አዎን፣ እናም የጌታ ድምፅ፣ በመልአኩ አንደበት፣ ለሀገር ሁሉ አውጇል፣ አዎን፣ በታላቅ ደስታ የምስራች ወሬ ይኖራቸው ዘንድ ያውጀዋል፤ አዎን፣ እናም በህዝቡ መካከል፣ አዎን፣ በምድር ፊት እስከዳርቻ ለተበተኑትም እንኳን፣ እነዚህን የምስራች እንዲሰሙ ያደርጋል፤ ስለዚህ እነዚህ ወደእኛ መጥተዋል።

፳፫ እናም እኛ እንድንረዳቸው ዘንድ፣ እንዳንሳሳት ዘንድ፣ በግልፅ አባባል እንድናውቃቸው ተደርገዋል፤ እናም ይህም የሆነው በባዕድ ምድር በመዘዋወራችን ነው፤ ስለዚህ፣ እኛ እነዚህን የምስራች ወሬዎች በወይን አትክልት ቦታዎቻችን ሁሉ ስለታወጁልን በይበልጥ ሞገስን አግኝተናል።

፳፬ እነሆም፣ መላዕክት በዚህ ጊዜ በምድራችን ላይ ለብዙዎች እያወጁ ናቸው፤ እናም የዚህም ዓላማ በክብሩ ለሚመጣበት ጊዜ የሰው ልጆችን ልብ ለማዘጋጀት ነው።

፳፭ እናም አሁን ስለእርሱ መምጣት በመላዕክት አንደበት የሚነገሩትን አስደሳች ዜና ለማዳመጥ ብቻ እየጠበቅን ነን፤ ጊዜው እየመጣ ነው፣ እንዴት እንደፈጠነ አናውቅም። በእኔ ቀናት እንዲሆን ዘንድ እግዚአብሔር ይፍቀደው፤ ነገር ግን በፍጥነት ወይም ዘግይቶ ቢሆን ይሁን፣ በእዚህም እደሰታለሁ።

፳፮ እናም ይህ በመልአኩ አንደበት፣ በሚመጣበት ጊዜ፣ እርሱን በተመለከተ በውስጣቸው በነበረው የትንቢት መንፈስ መሰረት የተናገሩት የአባቶቻቸው ቃላት እንደሚሟሉ ለእውነተኛና ለቅዱሳን ሰዎች እንዲታወቅ ይደረጋል።

፳፯ እናም አሁን፣ ወንድሞቼ፣ ከልቤ ውስጣዊ ቦታ፣ አዎን እስከህመም በሚሆን በታላቅ ጭንቀት፣ ቃሌን ታደምጡኝ ዘንድ፣ እናም ኃጢአታችሁን ታስወግዱና፣ የንስሃችሁን ጊዜ እንዳታዘገዩት እመኛለሁ

፳፰ ነገር ግን በጌታ ፊት ራሳችሁን ትሁት ታደርጉ ዘንድና፣ ቅዱስ ስሙን ትጠሩ ዘንድ፣ እናም ያለማቋረጥ እንድትተጉ እንዲሁም እንድትፀልዩ፣ ከሚቻላችሁ በላይም እንዳትፈተኑም፣ እናም ትሁት፣ የዋህ፣ ታዛዥ፣ ታጋሽ፣ ፍቅር የሞላባችሁና ፅኑ መከራን ቻይ በመሆን በመንፈስ ቅዱስ የምትመሩ እንድትሆኑ እመኛለሁ።

፳፱ በጌታ እምነት ይኑራችሁ፣ ዘለአለማዊ ህይወትን ለመቀበል በተስፋ የተሞላችሁ ሁኑ፣ በመጨረሻው ቀን ከፍ እንድትሉና ወደእረፍቱም እንድትገቡ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር ሁልጊዜም በልባችሁ ይሁን።

እናም ቁጣውን በላያችሁ ላይ እንዳታመጡ፣ በሲኦል ሰንሰለትም እንዳትታሰሩ፣ በሁለተኛ ሞትም እንዳትሰቃዩ፣ ጌታ ንስሃን ይስጣችሁ።

፴፩ እናም አልማ በዚህ መፅሐፍ ያልተፃፉ ከዚህ የበለጡትን ብዙ ቃላት ለህዝቡ ተናገረ።