ምዕራፍ ፲፭
ኢየሱስ የሙሴ ህግ በእርሱ እንደተፈፀም ተናገረ—ኔፋውያን በኢየሩሳሌም የተናገረላቸው ሌሎቹ በጎች ናቸው—በክፋታቸው የተነሳ፣ በኢየሩሳሌም ያሉ የጌታ ሰዎች ስለተበተኑት የእስራኤል በጎች አያውቁም። ፴፬ ዓ.ም. ገደማ።
፩ እናም እንግዲህ እንዲህ ሆነ ኢየሱስ ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ዐይኑን በዙሪያው ባሉ ሰዎች ላይ አሳረፈ፣ እናም እንዲህ አላቸው፥ እነሆ ወደ አባቴ ከማረጌ በፊት ያስተማርኩትን ነገሮች ሰምታችኋል፤ ስለዚህ፣ ይህንን ንግግሬን የሚያስታውስ እናም ሀየሚፈፅም በመጨረሻው ቀን ለአስነሳዋለሁ።
፪ እናም እንዲህ ሆነ ኢየሱስ እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ የሙሴን ሀህግ በተመለከተ ምን እንዲያደርጉ እንደሚፈልግባቸው የሚገረሙና፣ የሚደነቁ ጥቂቶች እንዳሉ አስተዋለ፤ አሮጌዎቹ ነገሮች እንዳለፉ እናም ሁሉም ነገሮች አዲስ እንደሆኑ የተነገሩትን አልተረዱምና።
፫ እናም እንዲህ ሲል ተናገራቸው፥ አሮጌዎቹ ነገሮች አልፈዋል፣ እናም ሁሉም ነገር አዲስ ሆነዋል ስላልኳችሁ አትገረሙ።
፬ እነሆ፣ ለሙሴ የተሰጠው ሀህግ ተፈፅሟል እላችኋለሁ።
፭ እነሆ፣ ህጉን የሰጠሁት ሀእኔ ነኝ፤ ከእስራኤል ህዝቦቼ ጋር ቃል ኪዳን የገባሁትም እኔ ነኝ፤ ስለዚህ ህጉን ልፈጽም ስለመጣሁ ህጉ በእኔ ለተፈፅሟል፤ ስለዚህ ይህም መጨረሻ አለው።
፮ እነሆ፣ ነቢያትን ሀአልሽርም፣ ምክንያቱም ብዙዎች በእኔ አልተፈፀሙምና፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ሁሉም ይፈፀማሉ።
፯ እናም አሮጌዎቹ ነገሮች ያልፋሉ ስላልኳችሁ፣ ስለሚመጡት ነገሮች ተነግረው የነበሩትን አልሽርም።
፰ እነሆም፣ ከህዝቤ ጋር የገባሁት ሀቃል ኪዳን በሙሉ አልተፈጸመም፤ ነገር ግን ለሙሴ የተሰጠው ህግ በእኔ መጨረሻ አለው።
፱ እነሆ፣ እኔ ሀህግ እንዲሁም ለብርሃን ነኝ። ወደ እኔ ተመልከቱ፣ እናም እስከመጨረሻው የጸናችሁ ሁኑ፣ እናም ሐህያው ትሆናላችሁ፤ እስከመጨረሻው መለሚፀናም የዘላለምን ህይወት እሰጠዋለሁና።
፲ እነሆ፣ ትዕዛዝን ሰጥቻችኋለሁ፤ ስለዚህ ሀትዕዛዜን ጠብቁ። እናም ህጉና ነቢያትም ይህ ነው፣ ስለእኔ በእውነት ለይመሰክራሉና።
፲፩ እናም እንግዲህ እንዲህ ሆነ ኢየሱስ እነዚህን ቃላት በተናገረበት ጊዜ፣ ለእነዚያ ለመረጣቸው አስራ ሁለቱ እንዲህ አላቸው፥
፲፪ እናንተ የእኔ ደቀመዛሙርት ናችሁ፤ እናም ሀለዮሴፍ ቤት ቅሪት ለሆኑትም ለእነዚህ ሰዎች ብርሃን ናችሁ።
፲፫ እናም እነሆ፣ ይህች ሀምድር የርስታችሁ ስፍራ ናት፣ እናም አብም ለእናንተ ይህን ሰጥቷችኋል።
፲፬ እናም በኢየሩሳሌም ለሚገኙት ወንድሞቻችሁ በማንኛውም ጊዜ ይህን ሀእንድናገር አብ ትዕዛዝ አልሰጠኝም ነበር።
፲፭ አብ ከምድሪቱ እንዲወጡ ስለመራቸው የእስራኤል ቤት ስለሆኑት ሀሌሎች ነገዶች በየትኛውም ጊዜ በኢየሩሳሌም ላሉት ወንድሞቻችሁ እንድናገር ትዕዛዝ አልሰጠኝም።
፲፮ አብም እስከዚህ ድረስ ለእነርሱ እንድናገራቸው አዞኛል፥
፲፯ ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ደግሞ ላመጣ ይገባኛል፣ ድምፄንም ይሰማሉ፣ አንድም መንጋ ይሆናሉ፣ ሀእረኛውም አንድ ይሆናል።
፲፰ እናም እንግዲህ፣ አንገተ ደንዳና በመሆናቸውና፣ ባለማመናቸው ቃሌን ሀሊረዱ አልቻሉም፤ ስለዚህ ይህን ነገር በተመለከተ ከዚህ የበለጠ እንዳልናገር በአብ ታዝዤ ነበር።
፲፱ ነገር ግን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በክፋታቸው የተነሳ እናንተ ከእነርሱ ተለይታችኋል ብዬ እነግራችሁ ዘንድ አብ አዞኛል፤ ስለዚህ በክፋታቸውም የተነሳ ነው ስለእናንተ የማያውቁት።
፳ እናም እንደገና እውነት እላችኋለሁ፣ ሌሎች ነገዶችን አብ ከእነርሱ ለይቷል፤ እናም በክፋታቸው የተነሳ ነው ስለእነርሱ የማያውቁት።
፳፩ እናም እውነት እላችኋለሁ፤ ከዚህም በረት ያልሆኑ ሀሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል፤ እነርሱም ድምጼን ይሰማሉ፤ እናም አንድ መንጋና፣ እረኛውም አንድ ይሆናል፣ በማለት የተናገርኩአችሁ እናንተ ናችሁ።
፳፪ እናም ሌሎቹ በጎች ሀአህዛብ ናቸው ብለው ስለገመቱ እኔን አልተረዱኝም፤ ምክንያቱም አህዛብ በእነርሱ ስብከት ለእንደሚለወጡ አልተረዱምና።
፳፫ እናም ድምፄን ያዳምጣሉ ማለቴንም አልተረዱም፤ እናም በማንኛውም ጊዜ ሀአህዛብ ድምፄን መስማት እንደማይችሉ፣ ለበመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ካልሆነም በቀር ራሴን እንደማልገልፅላቸውም አልተረዱኝም።
፳፬ ነገር ግን እነሆ፣ ሀድምፄን ሰምታችኋልም፣ አይታችሁኛልም፤ እናንተም የእኔ በጎች ናችሁ፤ እናም አብ ለእኔ ለከሰጣቸው መካከልም የተቆጠራችሁ ናችሁ።