ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፱


ምዕራፍ ፱

አይሁዶች በቃልኪዳናቸው ምድር ላይ ሁሉ እንደሚሰበሰቡ ያዕቆብ ገለጸ—የኃጢያት ክፍያው ለሰው ከውድቀት ቤዛ ይሆናል—የሙታን አካል ከመቃብር እንዲሁም መንፈሳቸው ከሲኦልና ከገነት ይመጣል—ይፈረድባቸዋል—የኃጢያት ክፍያው ከሞት፣ ከሲኦል፣ ከዲያብሎስ፣ ማለቂያ ከሌለው ስቃይ ያድናል—ፃድቃን በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ይድናሉ—የኃጢያት ቅጣቶች ተገልፆአል—የእስራኤሉ ቅዱስ የመግቢያው በር ጠባቂ ነው። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

እናም አሁን የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ጌታ ከእስራኤል ቤት ሁሉ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ታውቁ ዘንድ እኔ እነዚህን ነገሮች አንብቤአለሁ—

እናም እርሱ ከመጀመሪያው ጀምሮ፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ ወደ እውነተኛው ቤተ ክርስቲያንና ወደ እግዚአብሔር እቅፍ ደግመው እስከሚመጡ ድረስ፣ እነርሱ ወደ ቤታቸው ወደ ርስት ምድራቸው በሚሰበሰቡበትና የቃልኪዳናቸው ምድር ሁሉ በሚመሰርቱበት ጊዜ ለአይሁድ በቅዱስ ነቢያቱ አፍ እንደተናገረ አንብቤአለሁ።

እነሆ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እነዚህን ነገሮች ለእናንተ የምናገረው ጌታ እግዚአብሔር በልጆቻችሁ ላይ ባፈሰሰበት በረከት ምክንያት እንድትደሰቱና ራሳችሁን ለዘለዓለም እንድታነሱ ነው።

ከእናንተ ብዙዎቹ ወደፊት ስለሚመጡ ነገሮች ለማወቅ ብዙ እንደመረመራችሁ አውቃለሁ፤ ስለዚህ ስጋችን አርጅቶ ከዚያም እንደሚሞት እንደምታውቁም አውቃለሁ፣ ይሁን እንጂ፣ በአካላችን እግዚአብሔርን እናያለን።

አዎን፣ እኛ ከመጣንበት በኢየሩሳሌም ውስጥ ላሉት እራሱን በአካል እንደሚያሳይ እንደምታውቁ አውቃለሁ፤ በእነርሱ መካከል ይህ መሆኑ አስፈላጊ ነውና፤ ምክንያቱም ታላቁ ፈጣሪው ሁሉም ሰዎች ለእርሱ ይገዙ ዘንድ እርሱ ለሰው ልጆች በስጋ ለመገዛት እንዲፈቅድና፣ ለሰዎች ሁሉ ይሞት ዘንድ አስፈላጊ ነበረበት።

ምህረት የተሞላበት የታላቁ የፈጣሪ ዕቅድ ይፈጸም ዘንድ፣ ሞት በሰው ልጆች ላይ ስለመጣ፣ የትንሣኤ ኃይል ይኖር ዘንድ ያስፈልጋል፣ በውድቀት የተነሳ ትንሣኤ ለሰው መምጣቱ አስፈላጊ ነው፣ እናም ውድቀት የመጣው በመተላለፍ ምክንያት ነው፤ እና ሰውም በመውደቁ ምክንያት ከጌታ ፊት ተለይቷል

ስለዚህ፣ ወሰን የሌለው የኃጢያት ክፍያ ይኖር ዘንድ ያስፈልጋል—በዚህ ወሰን በሌለው የኃጢያት ክፍያ ባይሆን ኖሮ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን አይለብስም ነበር። ስለዚህ፣ በሰው ላይ የመጣው የመጀመሪያው ፍርድ ለዘለዓለም የሚቆይ መሆን ነበረበት። እናም እንዲህ ቢሆን ኖሮ ይህ ስጋ ሞቶ፣ በስብሶ፣ ተበታትኖ ወደ እናት ምድሩ በመመለስ፣ በድጋሚ ሳይነሳ በቀረ ነበር።

አቤቱ የእግዚአብሔር ጥበብምህረቱና ፀጋው! እነሆም፣ ስጋ የማይነሳ ቢሆን ኖሮ መንፈሳችን ከዘለዓለማዊው አምላክ ፊት ተነጥሎ ዳግም እንዳይነሳ ከተጣለውና ዲያብሎስ ለሆነው መልአክ ተገዢዎች ይሆኑ ነበር።

እናም መንፈሶቻችን እንደርሱ ሊሆኑ በተገባቸው ነበር፣ እናም እኛ ዲያብሎሶች፣ ለዲያብሎስ መላእክቶች በመሆን ከአምላካችን ፊት የጠፋንናከሀሰት አባት ጋር፣ በችግር፣ ልክ እንደእርሱ የቀረን እንሆን ነበር፤ አዎን፣ በዚያ የመጀመሪያ ቤተሰቦቻችንን እንዳታለለው፣ እራሱን እንደብርሃን መልአክ እንዲመስል ራሱም እንደቀየረውና፣ የሰው ልጆችን በግድያ ሚስጥራዊ ሴራዎች እና በሁሉም የጨለማ ሚስጥር ስራዎች እንደሚበጠብጠው እንሆን ነበር።

አቤቱ፣ ከዚህ ከሚያስቀይመው አስፈሪ እቅፉ፣ አዎን፣ እኔ የስጋ ሞት፣ እናም ደግሞ የመንፈስ ሞት ብዬ የምጠራው ያ አስፈሪ ሞትና ሲኦልን ሊያስመልጠን መንገዱን ያዘጋጀልን የአምላካችን ጥሩነት እንዴት ታላቅ ነው።

፲፩ እናም የእኛ አምላክ የእስራኤል ቅዱስ ማምለጫውን መንገድ ስላዘጋጀልን፣ ጊዜያዊ የሆነው እኔ የተናገርኩት ይህ ሞት፣ ሙታኖቹን ያስረክባል፤ ይህም ሞት መቃብር ነው።

፲፪ እናም መንፈሳዊ ሞት የሆነው ይህ እኔ የተናገርኩት ሞት፣ ሙታኖቹን ያስረክባል፤ ይህም መንፈሳዊ ሞት ሲኦል ነው፤ ስለዚህ፣ ሞትና ሲኦል ሙታኖቻቸውን ማስረከብ አለባቸው፣ እናም ሲኦል የያዛቸውን መንፈሶች ማስረከብ አለበት፣ መቃብርም የያዘቻቸውን አካላት ማስረከብ አለባት፣ እናም የሰዎች ስጋና መንፈስ አንዱ ወደ ሌላው ደግሞ ይመለሳል፤ ይህም በእስራኤል ቅዱስ የትንሳኤ ሀይል ነው።

፲፫ አቤቱ የአምላካችን ዕቅድ እንዴት ታላቅ ነው! በሌላው በኩል፣ የእግዚአብሔር ገነት የቅዱሳንን መንፈስ ማስረከብ አለባት፤ መቃብርም የፃድቃንን ስጋ ታስረክባለች፤ እናም ስጋና መንፈስ እንደነበሩ በድጋሚ ይገጣጠማሉ፣ ሁሉም ሰዎች የማይበሰብሱና፣ የማይሞቱ ይሆናሉ፣ እና የእኛም እውቀት ፍፁም ከመሆኑ በቀር፣ እነርሱም ልክ እንደእኛ በስጋ ፍፁም እውቀት ያላቸው ነፍሳት ይሆናሉ።

፲፬ ስለዚህ፣ ስለስህተቶቻችን ሁሉና፣ ንፁህ አለመሆናችንን፣ እናም ስለራቁትነታችን ፍፁም እውቀት ይኖረናል፤ ጻድቃንም ንፅህናን ለብሰው የጽድቅ መጎናፀፊያ ተደርቦላቸው ስለደስታቸውና ጻድቅነታቸው ፍፁም እውቀት ይኖራቸዋል።

፲፭ እናም እንዲህ ይሆናል ሁሉም ሰዎች ከዚህ ከመጀመሪያው ሞት ወደ ሕይወት ሲያልፉና፣ ህያዋን ሲሆኑ፣ በእስራኤል ቅዱስ የፍርድ ወንበር ፊት መምጣት አለባቸው፤ እናም ከዚያ ፍርዱ ይመጣል፣ ከእዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ቅዱስ ፍርድ መሰረት ይፈረድባቸው ይገባል።

፲፮ እናም በእርግጥ፣ ጌታ ህያው እንደሆነ፣ ጌታ አምላክ ተናግሮታልና፣ እናም ይህ የእርሱ ሳይከናወን የማይቀር ዘለዓለማዊ ቃሉ ነው፣ ፃድቅ የሆኑት አሁንም ፃድቅ ይሆናሉ፣ የረከሱትም አሁንም ርኩሳን ይሆናሉ፤ ስለዚህ፣ የረከሱት ዲያብሎስና መላዕክቱ ናቸው፤ እነርሱም ደግሞ ለእነርሱ ወደ ተዘጋጀላቸው ወደ ዘለዓለማዊ እሳት ይሄዳሉ፤ እናም ስቃያቸው እሳቱ ወደላይ ለዘለዓለም እንደሚነሳ ወላፈን፣ መጨረሻ እንደሌለው በዲን እንደሚቃጠል የእሳት ባህር ይሆናል።

፲፯ አቤቱ የአምላካችን ፍትህና ታላቅነት እንዴት ታላቅ ነው! እርሱ ቃሉን ሁሉ ይፈፅማል፣ እነርሱም ከአፉ ወጥተዋል፣ እናም የእርሱ ህግ መፈፀም አለበት።

፲፰ ነገር ግን፣ እነሆ፣ ፃድቃን፣ የእስራኤሉ ቅዱሰ ቅዱሳኖች፣ በእስራኤሉ ቅዱስ ያመኑት፣ የዓለምን መስቀሎች የታገሱ፣ እፍረቷንም የናቁ፣ እነዚህ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ የተዘጋጀላቸውን የእግዚአብሔርን መንግስት ይወርሳሉ፣ እናም ደስታቸው ለዘለዓለም ሙሉ ይሆናል።

፲፱ አቤቱ የአምላካችን የእስራኤል ቅዱስ ታላቅነትና ምህረት እንዴት ታላቅ ነው! እርሱ ቅዱሳኑን ከሚያስቀይመው ከአስፈሪው ዲያብሎስና፣ ከሞትና፣ ከሲኦል፣ እናም ከዚያ መጨረሻ የሌለው ስቃይ ከሆነው በዲን ከሚቃጠለው የእሳት ባህር አድኗቸዋልና

አቤቱ የአምላካችን ቅዱስነት እንዴት ታላቅ ነው! እርሱ ሁሉን ነገሮች ያውቃልና፣ እናም እርሱ ከሚያውቀው በስተቀር ምንም ነገር የለም።

፳፩ እናም እርሱ ሰዎች ሁሉ የእርሱን ድምፅ የሚያዳምጡ ከሆነ ሊያድናቸው ዘንድ ወደ እዚህ ዓለም ይመጣል፤ እነሆም፣ እርሱ በሁሉ ሰዎችን ህመም፣ አዎን፣ በአዳም ቤተሰብ አባል በሆኑት በእያንዳንዱ ሕያው ፍጥረታት፣ በወንድም፣ በሴትም፣ በልጆችም ህመም ይሰቃያል።

፳፪ እናም እርሱ ይህን ሁሉ የሚሰቃየው ትንሣኤ በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ያልፍ ዘንድና፣ ሁሉም በእርሱ ፊት በታላቁና በፍርድ ቀን ይቆሙ ዘንድ ነው።

፳፫ እናም እርሱ ሁሉም ሰዎች፣ በእስራኤል ቅዱስ ፍፁም የሆነ እምነት ኖሯቸው ንስሀ መግባትና፣ በእርሱ ስም መጠመቅ እንዳለባቸው ያዝዛል፣ ካልሆነ ግን በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መዳን አይችሉም።

፳፬ እናም በእርሱ ስም የማያምኑና ንስሀ የማይገቡ፣ በስሙም የማይጠመቁና፣ እስከመጨረሻው የማይጸኑ ከሆነ ግን መኮነን ይገባቸዋል፤ ምክንያቱም ጌታ አምላክ የእስራኤል ቅዱስ ተናግሮታልና።

፳፭ ስለዚህ፣ እርሱ ህግን ሰጥቷል፤ እናም ህግ ባልተሰጠበት ቅጣት የለም፤ እናም ቅጣት በሌለበት ኩነኔ የለም፤ እናም መኮነን በሌለበት በኃጢያት ክፍያው የተነሳ የእስራኤል ቅዱስ ምህረት በእነርሱ ላይ ውጤታማ ይሆናል፤ ምክንያቱም በእርሱ ኃይል ድነዋልና።

፳፮ ከአስቀያሚ ከአስፈሪው ከሞትና ከሲኦል፣ እናም ከዲያብሎስና፣ መጨረሻ ከሌለው በዲን ከሚቃጠለው የእሳት ባህር ስቃይ ይተርፉ ዘንድ፣ ህጉ ባልተሰጣቸው ሁሉ ላይ የኃጢያት ክፍያው ለፍትህ የሚያስፈልገውን ሁሉ ያደርጋል፤ እናም እስትንፋስ ወደሰጣቸው እስራኤሉ ቅዱስ ወደሆነው እግዚአብሔር ይመለሳሉ።

፳፯ ነገር ግን ህጉ ለተሰጠው፣ አዎን፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ልክ እንደ እኛ ያለው፣ እናም የሚተላለፋቸውና፣ የሙከራውን ጊዜ የሚያባክን ወዮለት፣ መጨረሻው አሰቃቂ ነውና!

፳፰ አቤቱ የክፉ የብልጠት ዕቅድ! አቤቱ የሰው ግብዝነትና ድክመትና፣ ሞኝነት! በተማሩ ጊዜ ራሳቸውን እንደብልህ ይቆጥራሉ፣ እናም የእግዚአብሔርን ምክር የማይሰሙ፣ በራሳቸው እንደሚያውቁ በማሰብ፣ ይህን ችላ ይሉታልና፣ ስለሆነም ጥበባቸው ሞኝነታቸው ነው እና አይጠቅማቸውም። እነርሱም ይጠፋሉ።

፳፱ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ምክሮች የሚያደምጡ ከሆነ መማር ጥሩ ነው።

ነገር ግን በዓለም ሀብት ሀብታም ለሆኑት ወዮላቸው። ሀብታም በመሆናቸው ድሆችን ይጠላሉና፣ ትሁቶችን ያሳድዳሉና፤ ልባቸውም በሀብታቸው ላይ ነውና፤ ስለዚህ፣ ሀብታቸው አምላካቸው ነው። እናም እነሆ፣ ሀብታቸው ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይጠፋል።

፴፩ እናም መስማትን ለማይፈልጉ ለደንቆሮዎች ወዮላቸው፤ ይጠፋሉና።

፴፪ ማየትንም ለማይፈልጉ ለዕውሮች ወዮላቸው፤ እነርሱም ደግሞ ይጠፋሉና።

፴፫ ልባቸውን ላልተገረዙት ወዮላቸው፣ የኃጢአታቸው እውቀት በመጨረሻው ቀን ይጎዳቸዋልና።

፴፬ ለውሸታም ወዮለት፣ ወደታች ወደ ሲዖል ይጣላልና።

፴፭ እያወቀ ለሚገድል ለነፍሰ ገዳይ ወዮለት፣ ይሞታልና

፴፮ ለሚያመነዝሩ ለአመንዝራዎች ወዮላቸው፣ ወደታች ወደ ሲኦል ይጣላሉና።

፴፯ አዎን፣ ጣኦትን ለሚያመልኩ ወዮላቸው፣ የዲያብሎሶች ሁሉ ዲያብሎስ በእነርሱ ይደሰትባቸዋልና።

፴፰ እናም፣ በአጠቃላይ፣ በኃጢአታቸው ለሚሞቱ ሁሉ ወዮላቸው፤ ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉና፣ እናም ፊቱን ያያሉ፣ በኃጢአታቸውም ይቀራሉ።

፴፱ አቤቱ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ቅዱስ የሆነውን እግዚአብሔርን መተላለፍ እንዴት መጥፎ እንደሆነ፣ እናም ደግሞ ለዚያ ለተንኮለኛ ፈተናዎች መጋለጥ እንዴት አስቀያሚ እንደሆነ አስታውሱ። ስለዓለም ማሰብ ሞት እንደሆነና፣ ስለመንፈሳዊ ነገር ማሰብ ዘለዓለማዊ ህይወት እንደሆነ አስታውሱ።

አቤቱ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ቃሌን አድምጡ። የእስራኤሉን ቅዱስ ታላቅነት አስታውሱ። እኔ በእናንተ ላይ ከባድ ነገሮችን እንደተናገርኩ አትበሉ፤ ይህንንም ካላችሁ፣ እውነትን ትቃወማላችሁ፤ እኔ የእናንተን ፈጣሪ ቃላት ተናግሬአለሁና። የእውነት ቃላት ንፁህ ላልሆኑ ሁሉ ላይ አስቸጋሪ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ነገር ግን ጻድቆች አይፈሯቸውም፣ እውነትን ይወዳሉና እናም አይጨነቁም።

፵፩ ከዚያም አቤቱ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ወደ ጌታ ወደ ቅዱሱ ። መንገዱ ፅድቅ እንደሆነ አስታውሱ። እነሆ፣ ለሰው መንገዱ ጠባብ ነው፣ ነገር ግን በእርሱ ፊት በቀጥተኛ አቅጣጫ ይጓዛል፣ መግቢያውን ጠባቂ የእስራኤሉ ቅዱስ ነው፤ እናም እርሱ በዚያ ቦታ ምንም አገልጋይ አይቀጥርም፤ እናም በመግቢያው ካልሆነ በቀር ምንም ሌላ መንገድ የለም፤ እርሱ ሊታለል አይችልምና፣ ጌታ አምላክ የእርሱ ስም ነውና።

፵፪ እናም ለሚያንኳኳ ሁሉ ለእርሱ ይከፍትለታል፤ እና ብልሆችም፣ የተማሩትና፣ ሀብታም ለሆኑት፣ በትምህርታቸው፣ በጥበባቸውና በሀብታቸው ኩራት ከፍ ያሉ—አዎን፣ እነርሱን ነው እርሱ የሚጠላው፤ እናም እነዚህን ነገሮች ካልጣሉም፣ እራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት ሞኞች አድርገው ካላሰቡና፣ ራሳቸውን በጥልቅ ትህትና በጣም ዝቅ ካላደረጉ፣ ለእነርሱ አይከፍትላቸውም።

፵፫ ነገር ግን የብልሆችና የአስተዋዮች ነገሮች—አዎን፣ ለቅዱሳን የተዘጋጀው ያ ደስታ፣ ከእነርሱ ለዘለዓለም ይደበቃሉ

፵፬ አቤቱ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ቃላቴን አስታውሱ። እነሆ፣ ካባዬን አውልቄ በፊታችሁ አራግፈዋለሁ፤ የመዳኔ አምላክ ሁሉን በሚያይ ዐይኑ እንዲመለከተኝ እፀልያለሁ፤ ስለዚህ፣ ሁሉም ሰዎች እንደስራቸው በሚፈረድባቸው በመጨረሻው ቀን፣ የእስራኤል አምላክ ኃጢአታችሁን ከላዬ ላይ እንዳወረድኩ፣ እናም በእርሱ ፊት በክብር እንደምቆምና ከደማችሁ ንፁህ እንደሆንኩ እንደሚመሰክር ታውቃላችሁ።

፵፭ አቤቱ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ከኃጢአታችሁ ተመለሱ፤ አጥብቆ ከሚያስራችሁ የእርሱን ሰንሰለት በጥሱ፤ ወደ መዳናችሁ ዓለት ወደሆነው እግዚአብሔር ኑ።

፵፮ ለዚያ የፍርድ ቀን ለሆነው፣ ፍትህ ለፃድቃን ለሚሰጥበት ለዚያ ለታላቁ ቀን በአሰቃቂ ፍርሃት እንዳትሸማቀቁ፣ ኃጢአታችሁን በፍፁም መልኩ እንዳታስታውሱ፣ እናም በታላቅ ድምፅ፥ ቅዱስ ቅዱስ ነው ፍርድህ፣ አቤቱ ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ—ነገር ግን ኃጢአቴን አውቃለሁ፤ ህግህን ተላልፌአለሁ፣ መተላለፎቼም የእኔው ናቸው፤ እናም ዲያብሎስ እኔን ይዞኛል፣ ስለዚህ እኔ የእርሱ ጉዳት የደረሰብኝ የመከራው ተሳዳጅ ነኝ በማለት ለመናገር እንድትገፋፉ ነፍሳችሁን አዘጋጁ።

፵፯ ነገር ግን እነሆ፣ ወንድሞቼ፣ ስለእነዚህ መጥፎ ነገሮች እውነታ እንድትነቁ ዘንድ ማድረጌ አስፈላጊ ነውን? አዕምሮአችሁ ንፁህ ቢሆን ኖሮ እኔ ነፍሶቻችሁን አሰቃይ ነበርን? ከኃጢአታችሁ ንፁህ ብትሆኑ ኖሮ በእውነቱ ግልፅነት እኔ ለእናንተ ግልፅ እሆን ነበርን?

፵፰ እነሆ፣ ቅዱሳን ብትሆኑ ኖሮ እኔ ስለቅዱስነት እነግራችሁ ነበር፤ ነገር ግን እናንተ ቅዱስ ስላልሆናችሁ፣ እና እኔን እንደአስተማሪ ስለአያችሁኝ፣ ስለኃጢያት ውጤት አስተምራችሁ ዘንድ አስፈላጊ ነው።

፵፱ እነሆ፣ ነፍሴ ኃጢያትን ትጠላለች፣ ልቤ ደግሞ በጻድቅነት ትደሰታለች፤ እናም የቅዱስ አምላኬን ስም አሞግሳለሁ

ወንድሞቼ ሆይ፣ ኑ፣ የተጠማችሁ ሁሉ፣ ወደ ውኃው ኑ፤ እና ገንዘብ የሌላችሁ፣ ኑ ግዙና ብሉ፤ አዎን፣ ኑ ወይንና ወተት ያለገንዘብና ያለዋጋ ግዙ።

፶፩ ስለዚህ፣ ዋጋ በሌለው ነገር ገንዘብ አታባክኑ፣ ወይንም አጥጋቢ ለማይሆን ጉልበታችሁን አታባክኑ፣ እናም አድምጡኝ፣ የተናገርኳቸውንም ቃል አስታውሱ፤ ወደ እስራኤሉ ቅዱስ ኑ፣ እናም የማይጠፋውን ሊበላሽ የማይቻለውን ተመገቡና፣ ነፍሳችሁ በመፋፋት ትደሰት።

፶፪ እነሆ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ የአምላካችሁን ቃላት አስታውሱ፤ ያለማቋረጥ በቀን ለእርሱ ፀልዩ፣ እናም በመሸ ጊዜ ለቅዱስ ስሙ ምስጋናን አቅርቡ። ልባችሁም ትደሰት።

፶፫ እናም እነሆ የጌታ ቃል ኪዳን እንዴት ታላቅ ነው፣ እናም ለሰው ልጆች እራሱን ዝቅ ማድረጉ እንዴት ታላቅ ነው፤ በታላቅነቱ፣ በጸጋውና በምህረቱ የተነሳ ለእኛ ዘራችንን በሙሉ በስጋ እንደማይጠፋ፣ ነገር ግን እንደሚጠብቃቸው ቃል ገብቶልናል፤ በሚመጡትም ትውልዶች በእስራኤል ቤት የተቀደሰ ቅርንጫፍ ይሆናሉ።

፶፬ እናም አሁን፣ ወንድሞቼ ሆይ፣ ለእናንተ የበለጠ እናገራለሁ፤ ነገር ግን በማግስቱ የተቀሩትን የእኔን ቃላት እገልፅላችኋለሁ። አሜን።