ምዕራፍ ፭
ኔፋውያን እራሳቸውን ከላማናውያን ለዩ፣ የሙሴን ህግ ጠበቁ፣ እናም ቤተመቅደስ ሰሩ—ላማናውያን ባለማመናቸው ከጌታ ፊት ተለዩ፣ ተረገሙ፣ እናም ለኔፋውያን እንደ ጅራፍ ሆኑ። ከ፭፻፹፰–፭፻፶፱ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እነሆ፣ እንዲህ ሆነ፣ እኔ ኔፊ፣ በወንድሞቼ ሀቁጣ የተነሳ ወደ ጌታ አምላኬ በጣም ጮህኩ።
፪ ነገር ግን እነሆ፣ እነርሱ ህይወቴን ለማጥፋት እስከመፈለጋቸው ድረስ በእኔ ላይ ቁጣቸው በርትቶ ነበር።
፫ አዎን፣ በእኔ ላይ እንዲህ ሲሉ አጉረመረሙ—ታናሽ ወንድማችን በእኛ ላይ ሀገዢ ለመሆን ያስባል፤ እናም እኛ በእርሱ ምክንያት ብዙ ችግር አጋጥሞናል፤ ስለዚህ፣ በእርሱ ቃል የተነሳ በተጨማሪ አንዳንሰቃይ አሁን እንግደለው። እነሆም እርሱ ገዢያችን እንዲሆን አንፈቅድም፤ ምክንያቱም ታላቅ ወንድሞቹ የሆንነው በዚህ ህዝብ ላይ መግዛት የሚገባን እኛ ነንና።
፬ አሁን በእነዚህ ሰሌዳዎች ላይ በእኔ ላይ ያጉረመረሙትን ቃል ሁሉ አልፅፍም። ነገር ግን እነርሱ ህይወቴን ሊያጠፉ ፈልገዋል የሚለውን ብቻ ማለት ይበቃኛል።
፭ እናም እንዲህ ሆነ፣ እኔ ሀኔፊ፣ እንዲሁም ከእኔ ጋር የሚሄዱት ሁሉ፣ ከእነርሱ መሸሽና ወደ ምድረበዳው መሄድ እንዳለብን ጌታ ለአስጠነቀቀኝ።
፮ ስለዚህም፣ እንዲህ ሆነ እኔ ኔፊ ቤተሰቤን፣ እናም ደግሞ ሀዞራምንና ቤተሰቡን፣ እናም ታላቅ ወንድሜን ሳምንና ቤተሰቦቹን፣ እናም ያዕቆብን እና ዮሴፍን፣ ታናናሽ ወንድሞቼን እናም ደግሞ እህቶቼን፣ እና ከእኔ ጋር የሚሄዱትን ሁሉ ወሰድኩ። እናም ከእኔ ጋር የሚሄዱት ሁሉ የእግዚአብሔርን ለማስጠንቀቂያዎችንና ራዕይ ያመኑ ነበሩ፤ ስለዚህ፣ የእኔን ቃል አዳመጡ።
፯ እናም ድንኳናችንንና ለመውሰድ የምንችለውን ማናቸውንም ነገሮች ወሰድንና፣ በምድረበዳ ውስጥ ለብዙ ቀናት ተጓዝን። እናም ለብዙ ቀናት ከተጓዝን በኋላ ድንኳኖቻችንን ተከልን።
፰ እናም ህዝቤ የቦታውን ስም ሀኔፊ ብለን እንድንጠራው ፈለጉ፤ ስለዚህም ኔፊ ብለን ጠራነው።
፱ እናም ከእኔ ጋር የነበሩ ሁሉ እራሳቸውን የኔፊ ሀህዝብ ብለው ለመጥራት ወሰኑ።
፲ እናም በሁሉም ነገሮች ፍርዱን፣ ስርአቱንና፣ የጌታን ትዕዛዝ በሙሴ ሀህግ መሰረት በትጋት ለመጠበቅ ተቀበልን።
፲፩ ጌታም ከእኛ ጋር ነበር፣ እናም እጅግ በለፀግን፤ እህል ዘርተናል፣ እናም እንደገና በብዛት ሰብስበናልና። እናም የበግና የከብት መንጋንና ከሁሉም አይነት እንስሳት ማርባት ጀመርን።
፲፪ እናም ደግሞ እኔ ኔፊ ሀበነሀስ ሰሌዳዎች ላይ የተቀረፁትን መዝገቦች፣ እናም ደግሞ እንደተፃፈው ለአባቴ በጌታ እጅ የተዘጋጀውን ለኳስ ወይም ሐኮምፓሱን አመጣሁ።
፲፫ እናም እንዲህ ሆነ እኛ በይበልጥ መበልፀግ እንዲሁም በምድሪቱ ላይ መብዛት ጀመርን።
፲፬ እናም አሁን ሀላማናውያን ተብለው የሚጠሩት ህዝቦች በማንኛውም ሁኔታ እንዳይመጡብንና እኛን እንዳያጠፉን ዘንድ፣ እኔ ኔፊ፣ የላባንን ለጎራዴ ወሰድኩና በእርሱ አይነት ብዙ ጎራዴዎችን ሰራሁ፤ ምክንያቱም እነርሱ ወደ እኔና ልጆቼ እናም ህዝቤ ተብለው ወደተጠሩት ያላቸውን ጥላቻ አውቃለሁና።
፲፭ እናም ህዝቤን በብዛት ከሁሉም አይነት እንጨትና ሀብረት፣ እናም መዳብና ነሀስ፣ እና ብረትና ወርቅ፣ እና ብርና ከከበሩ የብረት አፈር ህንፃ እንዲሰሩ አስተማርኳቸው።
፲፮ እናም እኔ ኔፊ ሀቤተመቅደስን ሰራሁ፤ ከብዙ ለከከበሩ ነገሮች የተገነባ ባይሆንም፣ እንደ ሐሰለሞን ቤተመቅደስ አይነት ነበር የሰራሁት፤ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች በምድሪቱ ላይ አልተገኙም ነበርና፣ ስለዚህ፣ እንደ ሰለሞን አይነት ቤተመቅደስ መስራት አልተቻለም። ነገር ግን የቤተመቅደሱ አሰራር ከሰለሞን ቤተመቅደስ ጋር ተመሳሳይ ነበር፤ እናም አሰራሩ እጅግ ያማረ ነበር።
፲፯ እናም እንዲህ ሆነ፣ እኔ ኔፊ፣ ህዝቤ ሀታታሪ እንዲሆኑና በእጃቸውም እንዲሰሩ አደረግሁ።
፲፰ እናም እንዲህ ሆነ፣ እነርሱ እኔ ሀንጉሳቸው እንድሆን ፈለጉ። ነገር ግን እኔ ኔፊ፣ ለእነርሱ ንጉስ እንዲኖራቸው አልፈለግሁም፤ ይሁን እንጂ፣ በውስጤ ባለው ኃይል መሰረት ለእነርሱ አደረግሁ።
፲፱ እናም እነሆ፣ እኔ የእነርሱ ሀገዢና ለአስተማሪ እሆን ዘንድ ወንድሞቼን በተመለከተ ጌታ የተናገራቸው ቃላት ተፈፅመዋል። ስለዚህ፣ በጌታ ትዕዛዝ መሰረት እነርሱ ህይወቴን ለማጥፋት እስከሚያስቡበት ድረስ ገዢያቸውና አስተማሪያቸው ነበርኩኝ።
፳ ስለሆነም፣ ጌታ እንዲህ ያለኝ ቃሉ ተፈፅሟል—እነርሱ የአንተን ቃል ሀእስካላዳመጡ ድረስ ከጌታ ፊት ይለያሉ። እናም እነሆ፣ እነርሱ ከፊቱ ለተለይተው ነበር።
፳፩ እናም እርሱ በኃጢአታቸው የተነሳ ሀእርግማን፣ አዎን፣ እንዲያውም ከባድ እርግማን፣ በእነርሱ ላይ እንዲመጣ አድርጓል። እነሆም በእርሱ ላይ ልባቸውን አጠጠሩ፣ እንደ ድንጋይም ሆኑ፤ ስለዚህ፣ እነርሱ ነጭ እና ቆንጆ እንዲሁም ለያማሩ ስለነበሩ ለህዝቤ የሚስቡ እንዳይሆኑ ጌታ እግዚአብሔር ሐበቆዳቸው ላይ ጥቁረት እንዲመጣባቸው አደረገ።
፳፪ እናም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አለ—ለክፋቶቻቸው ንስሀ ካልገቡ በስተቀር ለህዝብህ ሀየሚያስጠሉ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ።
፳፫ እናም ከእነርሱ ዘር ጋር ሀየተቀላቀለው ዘር የተረገመ ይሆናል፤ እነርሱ በእንደዚህ አይነት እርግማን ይረገማሉ። እናም ጌታ ተናግሮታል፣ ይህም ተደርጓል።
፳፬ እናም በእነርሱ ላይ ባለው እርግማን የተነሳ ሀሰነፍ፣ አጭበርባሪዎችና በተንኮል የረቀቁ እንዲሁም በምድረበዳ ውስጥ አራዊቶችን የሚያድኑ ህዝቦች ሆነዋል።
፳፭ እናም ጌታ እግዚአብሔር አለኝ፥ እኔን ያስታውሱ ዘንድ ለማነሳሳት ለዘሮችህ እንደ ጅራፍ ይሆናሉ፤ እናም እኔን ካላስታወሱኝና፣ ቃሌንም ካላዳመጡ፣ እስከሚጠፉ ድረስ ይቀጧቸዋል።
፳፮ እናም እንዲህ ሆነ፣ እኔ ኔፊ፣ ያዕቆብንና፣ ዮሴፍን በህዝቤ ምድር ላይ ካህናትና መምህራን ይሆኑ ዘንድ ሀቀባኋቸው።
፳፯ እናም እንዲህ ሆነ አስደሳች ህይወት ኖርን።
፳፰ እናም ኢየሩሳሌምን ለቀን ከወጣን ሠላሳ ዓመታት አለፉ።
፳፱ እናም እኔ ኔፊ፣ ህዝቤን በተመለከተ በሰራሁት በሰሌዳዎች ላይ እስከዚያ ያለውን ታሪክ ጽፌ ጠበቅሁ።
፴ እናም እንዲህ ሆነ ጌታ እግዚአብሔር አለኝ፥ ሀሌሎች ሰሌዳዎችን ስራ፤ እናም ለህዝብህ ጥቅም በእኔ አመለካከት መልካም የሆኑትን ብዙ ነገሮች በእነዚህ ላይ ትፅፋለህ።
፴፩ ስለሆነም፣ እኔ ኔፊ፣ ለጌታ ትዕዛዛት ታዛዥ ለመሆን፣ ሄድኩ፣ እናም እነዚህን ነገሮች የፃፍኩበትን ሀእነዚህን ሰሌዳዎች ሰራሁ።
፴፪ እናም እግዚአብሔርን የሚያስደስተውን ቀረፅኩኝ። እናም ህዝቤ በእግዚአብሔር ነገር የሚደሰት ከሆነ በእነዚህ ሰሌዳዎች ላይ እኔ በቀረፅኩት ይደሰታሉ።
፴፫ እናም ህዝቤ የህዝቤን ታሪክ በጥልቀት ለማወቅ ከፈለጉ፣ የእኔን ሌሎች ሰሌዳዎች ማጥናት አለባቸው።
፴፬ እናም አርባ ዓመታት ዓለፉ ማለት ለእኔ በቂ ነው፣ እናም ከወንድሞቻችን ጋር በጦርነትና ፀብ አሳልፈናል።