ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፪


ምዕራፍ ፪

ቤዛነት በቅዱሱ መሲህ ይመጣል—የምርጫ ነፃነት (በራስ መነሳሳት) ለመኖርና ለማደግ አስፈላጊ ነው—ሰዎች ይኖሩ ዘንድ አዳም ወደቀ—ሰዎች ነፃነትን እና ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ ነፃ ናቸው። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።

ያዕቆብ፣ እናም አሁን እኔ እናገርሃለሁ፥ በምድረበዳ ውስጥ በመከራዬ ጊዜ አንተ የበኩር ልጄ ነህ። እናም እነሆ በወንድሞችህ መጥፎነት የተነሳ፣ በልጅነትህ ጊዜ በመከራና በብዙ ኃዘን ተሰቃይተሀል።

ይሁን እንጂ፣ ያዕቆብ፣ በምድረበዳ ውስጥ የተወለድክ የበኩር ልጄ፣ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ታውቃለህ፤ እናም እርሱ መከራህን ወደ ጥቅምህ ይለውጥልሃል።

ስለዚህ፣ ነፍስህ ይባረካል፣ እናም ከወንድምህ ኔፊ ጋር በደህና ትኖራለህ፤ እናም ቀናትህን አምላክህን በማገልገል ታሳልፋለህ። ስለዚህ፣ በቤዛህ ፅድቅ ምክንያት አንተ እንደምትድን አውቃለሁ፤ ምክንያቱም በዘመኑ ፍፃሜ ለሰዎች ደህንነትን ለማምጣት እርሱ እንደሚመጣ አይተሀልና።

እናም አንተ በወጣትነትህ የእርሱን ክብር አይተሀል፤ ስለዚህ፣ አንተ እርሱ በስጋውም እንኳን ሆኖ እንደሚያገለግላቸው የተባረክህ ነህ፤ ምክንያቱም መንፈስ ትላንትና፣ ዛሬና፣ ለዘለዓለም አንድ ነውና። እናም ከሰው ልጅ ውድቀት ጀምሮ መንገዱ ተዘጋጅቷል፣ ደህንነትም ነፃ ነው።

እናም ሰዎች መጥፎን ከጥሩው መለየትን ለማወቅ በብቃት ተምረዋል። እናም ህግ ለሰዎች ተሰጥቶአል። እና በህግ ማንም ስጋ አይጸድቅም፤ ወይም፣ በህግ ሰዎች ከእግዚአብሔር ተለይተዋል። አዎን፣ በጊዜያዊ ህግ እነርሱ ተለይተዋል፤ ደግሞም፣ በመንፈሳዊ ህግ ከጥሩው ይለያሉ፣ ለዘለዓለምም ጎስቋሎች ይሆናሉ።

ስለዚህ፣ ቤዛነት በቅዱሱ መሲህ እና በእርሱ አማካይነት ይመጣል፤ ምክንያቱም እርሱ በፀጋና በእውነት የተሞላ ነው።

እነሆ፣ እርሱ ልባቸው ለተሰበረ፣ እና መንፈሳቸው ለተዋረደ ሁሉ በህግ የተጠየቁትን ለማሟላት እራሱን ለኃጢያት መስዋዕት ያቀርባል፣ እናም በህግ የተጠየቀው ለሌላ ለማንም ሊመለስ አይቻልም።

ስለሆነም፣ የመጀመሪያው የትንሣኤ በመሆን፣ በስጋ በሞተው እናም ህይወቱን በመንፈስ ኃይል እንደገና በማንሳት ሙታን እንዲነሱ ባደረገው በቅዱሱ መሲህ መልካም ሥራና፣ ምህረትና ፀጋ በስተቀር፣ በእግዚአብሔር ፊት ማንም ስጋ ሊኖር እንደማይችል ያውቁ ዘንድ፣ እነዚህን ነገሮች ለምድር ነዋሪዎች እንዲያውቁት ማድረግ እንዴት ታላቅ ነገር ነው።

ስለዚህ እርሱ ለእግዚአብሔር የመጀመሪያው ፍሬ ነው፣ ሆኖም ለሰው ልጆች ሁሉ ያማልዳል፤ እናም እነዚያ በእርሱ ያመኑትም ይድናሉ።

እናም ለሁሉም በመማለዱ፣ ሁሉም ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ይመጣሉ፤ ስለዚህ፣ በውስጡ ባለው እውነትና ቅድስና መሰረት እንዲፈረድባቸው በፊቱ ይቆማሉ። ስለዚህ የተመደበውን ቅጣት ለመስጠት፣ የኃጢያት ክፍያውን መጨረሻ ለማሟላት ቅዱሱ አስፈላጊውን ህግ ሰጥቷል፣ ይህም የተመደበ ቅጣት ከተመደበው የደስታ ሽልማት ጋር ተቃራኒ ነው—

፲፩ ለሁሉም ነገሮች ተቃራኒ መኖር አስፈላጊ ነውና። ካልሆነ ግን በምድረበዳ ውስጥ የወለድኩህ የበኩር ልጄ፣ ፅድቅ፣ ኃጢያት፣ ቅድስና ወይም መከራ፣ ጥሩ ወይም መጥፎ መኖር አይችልም። ስለዚህ፣ ሁሉም ነገሮች በአንድነት ሊጣመሩ ይገባል፤ ስለዚህ፣ አንድ ሰውነት ብቻ ከሆነ፣ ሞትም ሆነ ህይወት፣ መበስበስም ሆነ አለመበስበስ፣ ደስታም ሆነ መከራ፣ መገንዘብም ሆነ አለማስተዋል ሳይኖረው፣ ሙት መሆን አለበት።

፲፪ ስለዚህ፣ ይህ ለማይረባ መፈጠር አለበት፤ ስለዚህ በመፈጠሩ በስተመጨረሻም ምንም ዓላማ ባልኖረውም ነበር። ስለዚህ፣ ይህ ነገር የእግዚአብሔርን ጥበብና የእርሱን ዘለዓለማዊ ዓላማውን፣ እናም ደግሞ ኃይሉን፣ ምህረቱን፣ እናም የእግዚአብሔርን ፍርድ ባጠፋውም ነበር።

፲፫ እናም እናንተ ህግ የለም የምትሉ ከሆነ፣ ኃጢያትም ደግሞ የለም ትላላችሁ። ኃጢያት የለም ካላችሁ፣ ፅድቅም ደግሞ የለም ትላላችሁ። እና ፅድቅ ከሌለ ደስታም የለም። እናም ፅድቅም ሆነ ደስታ ከሌለ ቅጣትም ሆነ መከራ አይኖርም። እናም እነዚህ ነገሮች ካልኖሩ እግዚአብሔር የለም። እናም እግዚአብሔር ከሌለ እኛም አንኖርም፣ መሬትም አትኖርም፣ የነገሮች ፍጥረት ሁሉ ሊሆን አይችልም፣ ምንም ነገር በማንኛውም ነገር ላይ ተፅዕኖ ሊያደርግ ወይም ተፅዕኖ ሊደረግበት አይችልምና፣ ስለዚህ፣ ሁሉም ነገሮች ሊጠፉ በተገባቸው ነበር።

፲፬ እናም አሁን ልጆቼ እኔ ለእናንተ ጥቅምና ግንዛቤ እነዚህን ነገሮች እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለ፣ እናም እርሱ ሁሉንም ነገሮች፣ ሰማያትንና ምድርንና፣ ተፅዕኖ የሚያደርጉ ወይም ተፅዕኖ የሚደረግባቸውን በእነርሱ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ነገሮች ፈጥሯል

፲፭ እናም ዘለዓለማዊ አላማውን ወደ ሰው ዘር የመጨረሻ ሁኔታ ለማምጣት፣ እርሱ የመጀመሪያ ወላጆቻችንንና የምድር አራዊትን፣ እናም የሰማይ አዕዋፋትንና፣ ባጠቃላይ የተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ከፈጠረ በኋላ፣ ተቃራኒ መኖሩ አስፈላጊ ነበር፤ እንዲሁም አንዱ ጣፋጭ ሲሆን ሌላኛው መራራ እንደሆነው የተከለከለውም ፍሬ እንደ ህይወት ዛፍ ተቃራኒ ነበር።

፲፮ ስለዚህ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሰው በራሱ እንዲያደርግ ሰጠው። ስለዚህ፣ ሰው በአንዱ ወይም በሌለኛው ካልተሳቡ በስተቀር ለራሱ ማድረግ አይቻለውም።

፲፯ እናም እኔ ሌሂ፣ ባነበብኳቸውና በተፃፈው መሰረት፣ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ እንደተጣለ እገምታለሁ፤ ስለዚህ፣ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ለማድረግ በመሞከር ዲያብሎስ ሆነ።

፲፰ እናም እርሱ ከሰማይ በመጣሉና፣ ለዘለዓአለም መከረኛ በመሆኑ፣ የሰውን ዘር በሙሉ በተመሳሳይ መከረኛ ለማድረግ ፈለገ። ስለዚህ፣ ለሔዋንም አዎን፣ ያ የቀደመው እባብ የሆነ ዲያብሎስ፣ የውሸት ሁሉ አባት እንዲህ አላት—ስለዚህ የተከለከለውን ፍሬ ብትመገቢ አትሞችም፣ ነገር ግን መልካሙንና መጥፎውን በማወቅ እንደ እግዚአብሔር ትሆኛለሽ አላት።

፲፱ እናም አዳምና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ ከበሉ በኋላ፣ መሬትን አርሰው ይበሉ ዘንድ ከዔድን ገነት ወጡ።

እናም ልጆችን ወለዱ፤ አዎን፣ የምድር ቤተሰቦችንም ሁሉ።

፳፩ እናም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በስጋ በነበሩበት ጊዜ ንስሀ ይገቡ ዘንድ የሰው ልጆች ዘመን ረጅም ነበር፤ ስለዚህ፣ ህይወታቸው የሙከራ ጊዜ ሆነ፣ እናም የሚኖሩበት ዘመን፣ ጌታ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች በሰጠው ትዕዛዛት መሰረት ተራዘመ። ሰዎች ሁሉ ንስሀ መግባት እንዳለባቸው ትእዛዝ ሰጥቶ ነበርና፤ ለሰዎች ሁሉ ወላጆቻቸው ህግን በመተላለፋቸው ምክንያት እንደጠፉ አሳይቷቸዋልና።

፳፪ እናም አሁን፣ እነሆ፣ አዳም ባይተላለፍ ኖሮ አይወድቅም ነበር፣ ነገር ግን በዔድን ገነት ይቆይ ነበር። እናም ሁሉም ተፈጥረው የነበሩ ነገሮች ከተፈጠሩ በኋላ በነበሩበት ሁኔታ መቆየት ነበረባቸው፤ እናም ለዘለዓለም በነበሩበት ሁኔታ መቆየት ነበረባቸው እናም መጨረሻ አይኖራቸውም ነበር።

፳፫ እናም እነርሱ ልጆች አይኖራቸውም ነበር፤ ስለዚህ በየዋህነት ይቆዩ ነበር፣ ደስታ አይኖራቸውም፣ መከራንም አያውቁምና፤ ኃጢያትን ባለማወቃቸው መልካምን አይሰሩም።

፳፬ ነገር ግን እነሆ፣ ሁሉም ነገሮች የተደረጉት ሁሉንም ነገሮች በሚያውቀው በጌታ ጥበብ ነው።

፳፭ ሰዎች እንዲኖሩ፣ አዳም ወደቀ፤ እና ሰዎች የሚኖሩትም ደስታም እንዲኖራቸው ዘንድ ነው።

፳፮ እናም መሲሁ የሰው ልጆችን ከውድቀት ለማዳን በዘመን ፍፃሜ ይመጣል። እናም እነርሱ ከውድቀት በመዳናቸው፣ መልካሙን ከመጥፎው ለይተው በማወቅ፣ በመጨረሻውና በታላቁ ቀን የህግ ቅጣት በስተቀር እግዚአብሔር በሰጠው ትዕዛዛት መሰረት የራሳቸውን ምርጫ ለማድረግና በሌለኛው ተፅዕኖ አንዳይደርስባቸውም ዘንድ ለዘለዓለም ነፃ ሆነዋል።

፳፯ ስለዚህ፣ ሰዎች በስጋ ባሉ ጊዜ ነፃ ናቸው፤ እናም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ሁሉ ለሰው ተሰጥተዋል። እናም እነርሱ ሁሉን ሰው በሚማልደው አማካኝነት ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ፣ ወይም እንደዲያብሎስ ምርኮና ሀይል ምርኮንና ሞትን ለመምረጥ ነፃ ናቸው፤ ምክንያቱም እርሱ ሰዎች ሁሉ እንደእርሱ መከረኛ እንዲሆኑ ይፈልጋል።

፳፰ እናም አሁን፣ ልጆቼ፣ በታላቁ አማላጅ እንድትመኩና ታላቅ ትዕዛዛቱን እንድትሰሙ፤ እናም ለቃሉ ታማኝ እንድትሆኑና፣ ዘለዓለማዊ ህይወትን በቅዱስ መንፈሱ ፈቃድ መሰረት እንድትመርጡ እፈልጋለሁ።

፳፱ እናም በስጋ ፈቃድ እንዲሁም፣ በራሱ መንግስት በእናንተ ይነግስ ዘንድ፣ የዲያብሎስን መንፈስ እናንተን ወደ ሲኦል እንዲወስዳችሁ ምርኮኛ የሚያደርግ ሀይል በሚሰጠው በውስጡ ባለው ክፋት መሰረት ዘለአለማዊ ሞት አትምረጡ።

ልጆቼ፣ እኔ እነዚህን ጥቂት ቃላት ሁሉ በመጨረሻው በሙከራዬ ጊዜ ተናግሬአችኋለሁ፤ እናም እኔ በነቢዩ ቃል መሰረት መልካሙን ክፍል መርጫለሁ። እናም እኔ ከነፍሳችሁ ዘለዓለማዊ ደህንነት በስተቀር ሌላ ምንም ዓላማ የለኝም። አሜን።