ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፲


ምዕራፍ ፲

አይሁድ አምላካቸውን እንደሚሰቅሉ ያዕቆብ ገለጸ—በእርሱም ማመን እስኪጀምሩም ድረስ ይበተናሉ—አሜሪካ ንጉስ የማይገዛባት የነፃ ምድር ትሆናለች— ራሳችሁን ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቁ፣ እናም በፀጋው መዳንን አግኙ። ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

እናም አሁን የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ እኔ ያዕቆብ ስለዚህ ስለተናገርኩት ስለተቀደሰው ቅርንጫፍ ደግሜ እናገራችኋለሁ።

እነሆም እኛ የያዝናቸው ቃልኪዳኖች ለስጋ የተገቡ ቃልኪዳኖች ናቸው፤ ስለዚህ፣ ብዙዎች ልጆቻችን እምነት በማጣታቸው የተነሳ እንደሚጠፉ ለእኔ ቢገለፀልኝም፣ ይሁን እንጂ፣ እግዚአብሔር ለብዙዎች ምህረትን ያወርዳል፤ እና ልጆቻችን የመድኃኒታቸውን እውነተኛ እውቀት ወደሚሰጣቸው ለመምጣት ደግመው ይመለሳሉ።

ስለዚህ፣ እንዳልኳችሁ፣ ክርስቶስ—ትናንት ማታ መልአኩ ስሙ ይህ እንደሚሆን ነግሮኛልና—ከአይሁዶች፣ በዓለም ከሌሎች በላይ ኃጢአተኛ በሆኑት፣ መካከል ይመጣል፤ እነርሱም ይሰቅሉታል—እንዲህ መሆኑ ለአምላካችን አስፈላጊ ነበርና፣ እናም በምድር ላይ የራሳቸውን አምላክ የሚሰቅል ሌላ ህዝብ የለም።

በሌሎች ሕዝቦች መካከል ታላቅ ተዓምራት ከተፈፀሙ ንስሀ ይገባሉ፣ እናም አምላካቸው እንደሆነ ያውቃሉ።

ነገር ግን በኃጢያትና በካህናት ተንኮል የተነሳ በኢየሩሳሌም ያሉት እርሱ እስኪገደል ድረስ እንኳ በእርሱ ላይ አንገተ ደንዳና ይሆናሉ።

ስለዚህ በኃጢአታቸው የተነሳ ጥፋት፣ ረሃብ፣ ቸነፈር፣ እና ደም መፍሰስ በእነርሱ ላይ ይመጣል፤ እናም የማይጠፉት ደግሞ በህዝቦች ሁሉ መካከል ይበተናሉ

ነገር ግን እነሆ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል—እኔ ክርስቶስ እንደሆንኩ፣ የሚያምኑበት ቀን በመጣ ጊዜ፣ ያኔ እኔ በስጋ ወደ ርስታቸው ምድር እመልሳቸው ዘንድ ከአባቶቻቸው ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ።

እናም እንዲህ ይሆናል፣ ከረጅም ዘመን ብተናቸው፣ ከባህር ደሴቶችና፣ ከምድር ከአራቱም ማዕዘናት ይሰበሰባሉ፤ እና አህዛቦች እነርሱን ወደ ርስት ምድራቸው በመውሰዳቸው የአህዛብ ሀገሮች በዐይኖቼ ፊት ታላቅ ይሆናሉ ይላል እግዚአብሔር።

አዎን፣ የአህዛብ ንጉሶች ለእነርሱ እንደ አባት ይሆኑላቸዋል፣ እናም ንግስቶቻቸውም እንደ እናቶች ይሆኑላቸዋል፤ ስለዚህ፣ ጌታ ለአህዛብ የገባው ቃል ኪዳን ታላቅ ነው፣ እርሱ ተናግሯታልና፣ እናም ማን ይቃወማል?

ነገር ግን እነሆ፣ ይህ ምድር፣ ይላል እግዚአብሔር፣ የርስታችሁ ምድር ይሆናል፣ እና አህዛብም በምድሩ ላይ የተባረኩ ይሆናሉ።

፲፩ እናም ይህ ምድር ለአህዛብ የነፃነት ምድር ይሆናል፣ እናም በምድሪቷም በአህዛብ ላይ የሚነሱ ንጉሶች አይኖሩም።

፲፪ እናም እኔ ይህንን ምድር ከሌሎች ሀገሮች አጠናክራቸዋለሁ።

፲፫ እናም ፅዮንን የሚዋጋ ይጠፋል፣ ይላል እግዚአብሔር።

፲፬ በእኔ ላይ ሌላ ንጉስ የሚያስነሳ ይጠፋልና፣ ምክንያቱም እኔ ጌታ የሰማይ ንጉስ፣ ንጉሳቸው እሆንላቸዋለሁ፣ እናም ድምፄን ለሚሰሙ ሁሉ ለዘለዓለም ብርሃን እሆንላቸዋለሁ።

፲፭ ስለዚህ፣ በዚህ የተነሳ፣ ለሰው ልጆች የገባኋቸው ቃልኪዳኖች ይፈፀሙ ዘንድ፣ እነርሱ በስጋ እያሉ አደርግላቸው ዘንድ፣ የጭለማ የሚስጥር ስራዎችንና፣ ግድያዎችን፣ እናም እርኩሰቶችን አጠፋ ዘንድ ያስፈልገኛል።

፲፮ ስለዚህ፣ አይሁድም ሆነ አህዛብ፣ ባርያም ሆነ ነፃ፣ ወንድም ሆነ ሴት፣ ፅዮንን የሚዋጋ ይጠፋል፤ የምድር ሁሉ ጋለሞታዎች እነዚህ ናቸውና፤ የእኔ ያልሆኑት ይቃወሙኛልና ይላል አምላካችን።

፲፯ ለሰው ልጆች በስጋቸው ላደርግላቸው የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈፅማለሁና

፲፰ ስለዚህ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ አምላካችን እንዲህ ይላል፣ ዘሮቻችሁን በአህዛብ እጅ አሰቃያለሁ፣ ይሁን እንጂ፣ እነርሱ እንደአባት ይሆኑላቸው ዘንድ የአህዛብን ልብ አራራለሁ፤ ስለዚህ፣ አህዛብ ይባረካሉ እናም ከእስራኤል ቤትም ውስጥ ይቆጠራሉ

፲፱ ስለዚህ፣ ለዘሮችህና ከዘሮችህ መሀል ለሚቆጠሩት ይህችን ምድር የርስት ምድራቸው ለዘለዓለም ትሆን ዘንድ እቀባታለሁ፤ እግዚአብሔርም ለእኔ ከሌሎች ምድሮች ሁሉ በላይ የተመረጠች ምድር ናት አለኝ፤ ስለዚህ፣ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ እኔን እንዲያመልኩ እፈልጋለሁይላል እግዚአብሔር።

እና አሁን፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ መሀሪው እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች በተመለከተ ታላቅ እውቀትን ስለሰጠን፣ እናስታውሰው፣ እናም ኃጢአታችንን እንተው፣ ተስፋም አንቁረጥ፣ እኛ አልተጣልንምና፤ ይሁን እንጂ፣ ከርስታችን ምድር እንድንወጣ ተደርገናል፤ ነገር ግን ወደተሻለ ምድር ተመርተናል፣ ጌታ ባህሩን መንገዳችን አድርጎልናል፣ እና በባህር ደሴት ላይ ነን።

፳፩ ነገር ግን በባህር ደሴቶች ላይ ላሉት የጌታ ቃል ኪዳን ታላቅ ነው፣ ስለዚህ ደሴቶች ስለሚል፣ ከዚህ የበለጡ ሌሎችም አሉ ማለት ነው፤ እናም እነርሱ ወንድሞቻችን የሚኖሩባቸው ናቸው።

፳፪ እነሆም ጌታ እግዚአብሔር እንደፈቃዱና እንደምኞቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከእስራኤል ቤት ህዝቡን አውጥቷል። እናም አሁን እነሆ፣ ጌታ የተገነጠሉትን ሁሉ ያስታውሳል፣ ስለዚህ እኛንም ደግሞ ያስታውሳል።

፳፫ ስለዚህ፣ ልባችሁን አስደስቱ፣ እናም በራሳችሁ ለመስራት፣ ዘለዓለማዊውን ሞት ወይም የዘለዓለማዊውን ህይወት መንገድ እራሳችሁ ለመምረጥ ነጻነት እንዳላችሁ አስታውሱ።

፳፬ ስለዚህ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ ራሳችሁን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር እንጂ ከዲያብሎስና ከስጋ ፈቃድጋር አታስታርቁ፤ እናም ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቃችሁ በኋላ የምትድኑት በእግዚአብሔር ፀጋ ውስጥና በእርሱ በኩል ብቻ እንደሆነ አስታውሱ።

፳፭ ስለዚህ፣ ወደዘለዓለም የእግዚአብሔር መንግስት እንድትገቡና፣ በመለኮታዊ ፀጋም እንድታመሰግኑት ዘንድ፣ እግዚአብሔር በትንሣኤ ኃይል ከሞት፣ እናም ደግሞ ከዘለዓለማዊው ሞት በኃጢያት ክፍያ ያንሳችሁ። አሜን።