ቅዱሳት መጻህፍት
፩ ኔፊ ፲፭


ምዕራፍ ፲፭

የሌሂ ዘሮች በኋለኛው ቀናት ከአህዛብ ወንጌልን ይቀበላሉ—የእስራኤልም መሰባሰብ የተፈጥሮ ቅርንጫፎቹ መልሰው እንደሚጣበቁ የወይራ ዛፍ ጋር ይመሳሰላል—ኔፊ የህይወት ዛፍን ራዕይ ተረጎመ እናም እግዚአብሔር ኃጢአተኛን ከፃድቅ ስለሚለያይበት ፍትህ ተናገረ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንዲህ ሆነ እኔ፣ ኔፊ፣ በመንፈስ ከተወሰድኩና እነዚህን ሁሉ ነገሮች ካየሁ በኋላ ወደአባቴ ድንኳን ተመለስኩ።

እናም እንዲህ ሆነ ወንድሞቼን ተመለከትኩ፣ እነርሱም አባቴ ለእነርሱ የተናገራቸውን ነገሮች በተመለከተ እርስ በእርሳቸው እየተከራከሩ ነበር።

ሰው ጌታን ካልጠየቀ በቀር ለመረዳት የሚያስቸግሩ ብዙ ታላቅ ነገሮችንም ነበር በእውነት ለእነርሱ ነግሯቸዋልና፤ እነርሱ በልቦቻቸው መጠጠር የተነሳ ማድረግ እንደነበረባቸው ወደጌታ አልተመለከቱም።

እናም አሁን እኔ ኔፊ በልባቸው ጠጣርነት፣ ደግሞም ባየሁአቸው ነገሮች ምክንያትና በሰዎች ልጆች ታላቅ ኃጢያት ምክንያት ሊወገዱ በማይችሉ መምጣት እንዳለባቸው ስላወቅሁ እጅግ አዘንኩ።

እናም እንዲህ ሆነ በራሴ ሀዘን ምክንያት ተሸነፍኩ፣ ምክንያቱም ውድቀታቸው እንዴት እንደሚሆን ስለተመለከትኩ፣ በህዝቤ ጥፋት ምክንያት የእኔ ሀዘን ከማንኛውም በላይ ታላቅ እንደነበር ተሰማኝ።

እናም እንዲህ ሆነ ጥንካሬን ካገኘሁ በኋላ ወንድሞቼን የክርክራቸው ምክንያት ምን እንደነበር ለማወቅ ተናገርኳቸው።

እናም እነሆ የተፈጥሮ ወይራ ዛፍን ቅርንጫፎችና፣ ደግሞም አህዛብን በተመለከተ አባታችን የተናገራቸውን ነገሮች ለመረዳት አንችልም አሉ።

እናም እንዲህ አልኳቸው፥ እናንተ ጌታን ጠይቃችኋልን?

እናም እንዲህ አሉኝ—አልጠየቅንም፣ ምክንያቱም ጌታ እኛን እንዲህ ያሉ ነገሮችን አያሳውቀንም።

እነሆ እነርሱን አልኳቸው—እንዴት ነው እናንተ የጌታን ትዕዛዝ የማትጠብቁት? እንዴት ነው በልባችሁ ጠጣርነት የተነሳ የምትጠፉት?

፲፩ ጌታ የተናገራቸውን ነገሮች አታስታውሱምን?—ልባችሁን ባታጠጥሩ እናም መልስ እንደምታገኙም በማመን ትዕዛዛቴን ለመጠበቅ በመትጋት በእምነት ብትጠይቁኝ፣ በእርግጥ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ግልፅ ይሆናሉ።

፲፪ እነሆ እላችኋለሁ የእስራኤል ቤት ከወይራው ዛፍ ጋር የተመሳሰለው በአባታችን ውስጥ በነበረው በጌታ መንፈስ ነበር፤ እናም እነሆ እኛ ከእስራኤል ቤት የተሰበርን አይደለንምን? ደግሞስ የእስራኤል ቤት ቅርንጫፎች አይደለንምን?

፲፫ እናም አሁን በአህዛብ ሙላት የተፈጥሮ ቅርንጫፎች መጣበቅ በተመለከተ አባታችን የተናገረው ነገር በኋለኛው ቀናት ዘሮቻችን እምነት በማጣት ሲመነምኑ፣ አዎን፣ ለብዙ ዓመታት፣ እንዲሁም መሲሁ ለሰዎች ልጆች እራሱን ከገለፀ ከብዙ ትውልዶች በኋላ፣ ከዚያም የመሲህ ወንጌል ሙሉነት ለአህዛብ፣ ከአህዛብም ወደ ዘሮቻችን ቅሪት ይመጣል—

፲፬ እናም በዚያ ቀን የዘሮቻችን ቅሪት ከእስራኤል ቤት መሆናቸውን፣ እነርሱም የጌታ የቃል ኪዳን ህዝቦች መሆናቸውን ያውቃሉ፤ ከዚያም እነርሱ ቅድመ አባቶቻቸው ወደማወቅ፣ ደግሞም በእርሱ አባቶቻቸው የተማሩትን የመድኃኒታቸውን ወንጌል ያውቃሉም፣ ለእውቀትም ይደርሳሉ፤ ስለዚህ እነርሱ ወደ መድኃኒታቸው እውቀትና፣ ወደእርሱ እንዴት እንደሚመጡና እንደሚድኑ ያውቁ ዘንድ ወደ ትምህርቱ እያንዳንዱ ነጠቦች በእውቀትም ይደርሳሉ።

፲፭ በዚያም ቀን አይደሰቱምን እና አለታቸውና አዳኛቸው ለሆነው ለዘለአለማዊው አምላክ ምስጋናን አያቀርቡምን? አዎን፣ በዚያ ቀን እነርሱ ከእውነተኛው ወይን ጥንካሬንና ጥቅም አያገኙምን? አዎን፣ ወደ እውነተኛው የእግዚአብሔር በረት አይመጡምን?

፲፮ እነሆ እላችኋለሁ፣ አዎን፣ እነርሱ በድጋሚ በእስራኤል ቤት መካከል ይታወሳሉ፤ ምክንያቱም የወይራ ዛፍ የተፈጥሮ ቅርንጫፎች በመሆናቸው ከእውነተኛው የወይራ ዛፍ ጋር ይጣበቃሉና

፲፯ አባታችንም ይህን ማለቱ ነው፤ እንዲሁም በአህዛብ እስከሚበተኑም ድረስ አይሆንም ማለቱ ነው፤ እና ማለቱም ጌታ ለአህዛብ ኃይሉን ያሳያቸው ዘንድ፣ ይህም በአህዛቦች አማካኝነት ይመጣል፣ ምክንያቱም በአይሁዶች ወይም እስራኤል ቤት ተቀባይነት አያገኝምና።

፲፰ ስለዚህ አባታችን ስለ እኛ ዘር ብቻ ሳይሆነ ነገር ግን ስለ እስራኤል ቤት ሁሉ ተናግሯል፣ በኋለኛው ቀን የሚፈፀመውን ቃል ኪዳን አመልክቷል፤ ይኸውም ጌታ ለአባታችን አብርሃም እንዲህ በማለት የገባው ቃል ኪዳን ነው፥ በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ።

፲፱ እናም እንዲህ ሆነ እኔ ኔፊ ለእነርሱ እነዚህን ነገሮች በተመለከተ ብዙ ተናገርኩ፤ አዎን፣ በኋለኛው ቀናት ስለአይሁዶች በዳግም መመለስን በሚመለከትም ለእነርሱ ተናገርኩ።

እናም ለእነርሱ ስለ አይሁዶች ወይም ስለ እስራኤል ቤት መመለስ ኢሳይያስ የተናገረውን ቃል፣ እንዲሁም እነርሱ ከተመለሱ በኋላ ከሌሎች ህዝቦች ጋር እንደማይቀላቀሉ፣ በድጋሚም እንደማይበተኑ አስረዳኋቸው። እናም እንዲህ ሆነ ለወንድሞቼ እንዲረጋጉና በጌታ ፊት እራሳቸውን ትሁት እንዲያደርጉ ብዙ ቃል ነገርኳቸው።

፳፩ እናም እንዲህ ሆነ በድጋሚ እንዲህ ሲሉ ተናገሩኝ—አባታችን በህልሙ ያየው ይህ ነገር ምን ማለት ነው? እርሱ ያየው ዛፍስ ምን ማለት ነው?

፳፪ እናም አልኳቸው—እሱ የህይወት ዛፍ ምልክት ነበር።

፳፫ እናም እንዲህ አሉኝ—ወደዛፉ የሚመራን አባታችን ያየው የብረት በትር ምን ማለት ነው?

፳፬ ይህም የእግዚአብሔር ቃል ነበር አልኳቸው፤ እናም የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰሙ ሁሉና፣ እርሱን አጥብቆ የያዘ በፍፁም አይጠፋም፤ ፈተናዎችና የጠላት ክፉ ፍላፃ እነርሱን ወደጥፋት ለመውሰድ በማሳወር ሊያሸንፏቸው አይችሉም።

፳፭ ስለዚህ እኔ ኔፊ የጌታን ቃል በጥብቅ እንዲያዳምጡ አበረታታኋቸው፤ አዎን፣ በውስጤ ባለው ኃይል ሁሉ እናም ባለኝ ችሎታ ሁሉ የጌታን ቃል በጥብቅ ያዳምጡ ዘንድ እንዲሁም በሁሉም ነገሮች ሁል ጊዜ ትዕዛዛቱን በመጠበቅ እንዲያስታውሱት መከርኳቸው።

፳፮ እናም ተናገሩኝ—አባታችን የተመለከተው የወንዙ ውሃ ምን ማለት ነው?

፳፯ እናም አባቴ ያየው ውኃ ርኩሱን ነገር ነበር አልኳቸው፤ አእምሮውም ሌሎች ነገሮችን በማሰብ የተሞላ ስለነበር የውሀውን ርኩስነት ልብ አላለውም ነበር።

፳፰ እናም ኃጢአተኞችን ከህይወት ዛፍ፣ እናም ደግሞ ከእግዚአብሔር ቅዱሳን የሚለያይ አሰቃቂ ገደል ነበር አልኳቸው።

፳፱ እናም ይህ የአሰቃቂው ሲኦል ምልክት ነበር፣ እርሱም መልአኩ እንደነገረኝ ለኃጢኣተኞች የተዘጋጀ ነበር አልኳቸው።

እናም አባታችን የእግዚእብሔር ፍትህ ደግሞ ኃጢአተኞችን ከፃድቃን እንደሚለይ እንዳየ፣ ድምቀቱም በመቀጠል ለዘለዓለም ወደ እግዚአብሔር እንደሚመጣና መጨረሻ እንደሌለው ልክ እንደነበልባል እሳት ደምቆ እንደነበር ነገርኳቸው።

፴፩ እናም እነርሱ ለእኔ አሉኝ—ይህ ነገር በምድር የሙከራ ጊዜያችን በሟች የሰውነታችን ስቃይ ማለት ነው፣ ወይስ ይህ ከጊዜያዊው ሰውነት ሞተ በኋላ የመጨረሻው የነፍስ ሁኔታ ማለት ነው፣ ወይስ የሚናገረው ነገር ጊዜያዊ ስለሆኑት ነገሮች ነው?

፴፪ እናም እንዲህ ሆነ እንዲህ አልኳቸው—ይህ ለጊዜያዊና ለመንፈሳዊ ነገሮች ምልክት ነበር፣ በስራዎቻቸው አዎን፣ እንዲሁም በሙከራ ጊዜያቸው በሟች ሰውነታቸው በተደረጉት ስራዎች፣ ሊፈረድባቸው ይገባል።

፴፫ ስለዚህ በኃጢኣታቸው የሚሞቱ ከሆኑ፣ ከፅድቅነት ጋር ከተገናኙ መንፈሳዊ ነገሮች መገለል ደግሞ ይገባቸዋል፤ ስለዚህ በስራቸው እንዲፈረድባቸውም በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መምጣት አለባቸው፤ እናም ስራቸው የረከሰ ከሆነ እነርሱም የረከሱ መሆን አለባቸው፤ የረከሱ ከሆኑም ደግሞ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር አይችሉም፤ እንዲህም ከሆነ፣ የእግዚአብሔር መንግስት ደግሞ የረከሰ መሆን አለበት።

፴፬ ነገር ግን እነሆ እላችኋለሁ የእግዚአብሔር መንግስት የረከሰ አይደለም፣ እናም ማንኛውም እርኩስ ነገር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም፤ ስለዚህ ርካሽ ለሆነው የተዘጋጀ የረከሰ ቦታ ሊኖር ይገባዋል።

፴፭ እናም የተዘጋጀ ቦታ፣ አዎን፣ እንዲሁም የተናገርኩት አሰቃቂው ገሀነም አለ፣ የዚህም አዘጋጅም ዲያብሎስ ነው፤ ስለዚህ የሰዎች ነፍሶች የመጨረሻ ሁኔታ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር፣ ወይም በተናገርኩት ፍትህ ምክንያት ወደውጭ መጣል ነው።

፴፮ ስለዚህ ኃጢአተኞች ከፃድቃን ጋር እናም ደግሞ ፍሬው እጅግ ያማረና ከሌሎች ፍሬዎች በላይ እጅግ ተፈላጊ ከሆነው የህይወት ዛፍ ይለያሉ፤ አዎን፣ ይህ ከእግዚአብሔር ስጦታዎች ሁሉ የበለጠ ነው። እንደዚህም ነበር ለወንድሞቼ የተናገርኩት። አሜን።