ሁሉም እንዲመጡ ተጋብዘዋል በአቅራቢያዎ ያለን ቤተክርስቲያንን ይጎብኙ።

እኛ ሌሎችን ለመውደድ እና ለማገልገል የተቻለንን የምናደርግ በክርስቶስ ላይ ያተኮርን ማህበረሰቦች ነን። እዚህ ለእርስዎ የሚሆን ቦታ አለ።
በአቅራቢያዎ የሚገኝ ቤተክርስቲያን ይፈልጉ።
People in Lima, Peru: Attending Church

የጋራ ጥያቄዎች

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ክርስቲያኖች ናቸውን?

አዎ! እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እና የአለም አዳኝ እንደሆነ እናምናለን። እርሱ ሁላችንም ከምናስበው በላይ ይወደናል። እኛ ራሳችንን የተሰጠን የኢየሱስ ተከታዮች አድርገን እንቆጥራለን። አንዳንድ እምነቶቻችን የተለዩ ቢሆኑም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወቱ፣ በአገልግሎቱ፣ በመስዋዕቱ እና በትንሣኤው ከኃጢአት፣ ከመከራ እና ከሞት እንደሚያድነን እናምናለን።

ስለእምነታችን የበለጠ ይማሩ።

የቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ምን ይመስላሉ?

የቤተክርስቲያን የአገልግሎት ጊዜ እንደየጉባኤው ይለያያል። ሆኖም ግን፣ ሁል ጊዜ ለሁሉም ሰው አንድ ዋና የአምልኮ አገልግሎት ሲኖር ከዚያም የልጆች፣ የወጣቶች እና ለአዋቂዎች የተዘጋጁ ክፍሎች አሉ።

ሁሉም ሰዎች የሚሳተፉበት አገልግሎት “የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ” ይባላል። ይህ ስብሰባ መዝሙሮችን፣ ጸሎቶችን እና በተለያዩ የቤተክርስቲያኗ አባላት የሚሰጡ ስብከቶችን (ወይም “ንግግሮችን”) ያካትታል። ሆኖም የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ እጅግ አስፈላጊው አካል ቅዱስ ቁርባንን መውሰድ ነው፣ ይህም በሌሎች የክርስቲያን ሃይማኖቶች ጋር ካለው ጌታን ለማስታወስ ከሚወሰደው (የጌታ እራት ጋር ተመሳሳይ ነው)።

ስለ እሁድ አገልግሎቶች የበለጠ ይወቁ ወይም በአቅራቢያዎ ያለ ቤተ ክርስቲያን ያግኙ።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቤተመቅደሶች ያሏት ለምንድነው?

ለኋለኛው ቀን ቅዱሳኖች ቤተመቅደስ ከሌሎች የቤተክርስቲያን ህንፃዎች የተለየ ነው። ቤተመቅደስ የኋለኛው ቀን ቅዱሳኖች ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ መመሪያን የሚያገኙበት ቦታ ነው። አባላት በቤተመቅደስ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳኖችን (ወይም ተስፋዎችን) ያደርጋሉ። ይህም ትእዛዛትን ለመጠበቅ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለመኖር፣ በትዳር ውስጥ ታማኝ ለመሆን እና ያለንን በማካፈል አንዳችን ሌላውን የመንከባከብ ቃልኪዳንን ያካትታል።

እንዲሁም፣ ቤተሰቦች ዘላለማዊ እንደሆኑ ስለምናምን በቤተመቅደስ ውስጥ የሚካሄደው አብዛኛው ስራ የቤተሰብ ትስስር የበለጠ ጠንካራ እንዲሆን ማድረግ ነው። በቤተመቅደስ ውስጥ የሚደረጉ ጋብቻዎች “እስከ ሞት ድረስ” ብቻ ሳይሆን ለዘለአለም የሚዘልቁ ናቸው። በቤተመቅደሶች ውስጥ ወላጆች እና ልጆች ዘላለማዊ ቤተሰቦች ይሆናሉ። ቀደምት አያቶቻችን አንድ ሰው ቅዱሳት ስርአቶችን ስለእነርሱ ከፈጸመ እና ያንን የአገልግሎት ተግባር ከተቀበሉ ሁሉንም የቤተመቅደስ በረከቶች ሊያገኙ ይችላሉ። ቤተመቅደሶች ስራ የሚበዛባቸው ቦታዎች ናቸው!

መፅሐፈ ሞርሞን ምንድን ነው?

መፅሐፈ ሞርሞን ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያስተምረን በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ቅዱስ መጽሐፍ ነው። ለግል ህይወታችን መመሪያን እንድንቀበል እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንቀርብ ይረዳናል። ስሙ የመጣው ከየት ነው? ከመቶ አመታት በፊት፣ ሞርሞን የተባለ አንድ ጥንታዊ ነቢይ የህዝቡን ዘገባ አሰባስቦ አጠናቀረ። እኛ የሚገጥሙንን አይነት ብዙ ተመሳሳይ ፈተናዎች ይገጥማቸው ነበር። ልክ እንደ እኛ፣ እነርሱም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመለሱ ብርታትን አግኝተዋል። ስለ መጽሐፈ ሞርሞን ከሚስዮናውያን መግቢያ ያግኙ

መፅሐፈ ሞርሞን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በአንድነት እንደ ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት እና እርሱ አዳኝ እና የአለም ቤዛ ስለመሆኑ መለኮታዊ ተልዕኮ ምስክርነት ነው። በአንድነት፣ መጽሐፍ ቅዱስ እና መፅሐፈ ሞርሞን የእግዚአብሔርን ታላቅ ፍቅር ለሁላችንም ይሰጡናል እንዲሁም ወደ እርሱ እንድንቀርብ ሊረዱን ይችላሉ። 

መጽሐፍ ቅዱስ እና መጽሐፈ ሞርሞን አብረው እንዴት እንደሚሠሩ የበለጠ ይማሩ።

በመጽሐፍ ቅዱስ እናምናለንን?

አዎን መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው፣ የተቀደሰ የቅዱሳት መጻሕፍት ጥራዝ ነው፣ ትምህርቶቹንም መከተል በሕይወታችን ውስጥ ደስታን ያመጣል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ልዩ በሆኑ ሌሎች የቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ መነሳሳትንም እንዲሁ እናገኛለን። ስለ እግዚአብሄር እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስፈላጊ የሆኑ እውነቶችን ለማስተማር ሁሉም በአንድነት ይሠራሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስላለን እምነት የበለጠ ይማሩ።

ተጨማሪ ይመልከቱ

ወደ እግዚአብሄር ቅረቡ ከሚስዮናዊያን ጋር ተገናኙ

በመስመር ላይ ወይም በአካል ተገናኙ። ለጥያቄዎችዎ መልስ እንሰጣለን እንዲሁም ከአካባቢያችሁ ቤተክርስቲያን ማህበረሰብ ጋር እናስተዋውቃችኋለን።

ለጉብኝት ይጠይቁ
Two sister missionaries prepare to ride the subway in Hong Kong

ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ፍጹሙ ምሳሌያችን

“ሁሉንም መውደድ እንዲሁም ለሁሉም መልካም ማድረግ አለብን። በሁሉም ግንኙነቶቻችን ውስጥ አለመግባባቶችን ማስወገድ እና አስታራቂዎች መሆን አለብን። ይህ የእኛን መርሆች እና ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ነገሮች ማላላት ሳይሆን ሌሎችን በኃይል ማጥቃትን ማቆም ማለት ነው። ፍጹሙ ምሳሌያችን በአገልግሎቱ ያደረገው ይህንኑ ነው። እርሱን እንድንከተለው ሲጋብዘን ለእኛ የተወው ምሳሌ ይህ ነው።"
Leon Parson will be doing a painting of President Oaks and has requested photos of President Dallin H. Oaks as reference
ፕሬዘደንት ዳልን ኤች. ኦክስ
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነቢይ እና ፕሬዚዳንት።

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያተኮረ የእምነት ማህበረሰብ

Four Corners: Primary Children
በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚጠበቁ ነገሮች
ቤተክርስቲያን ከዕለት ተዕለት የሕይወት ትርምስ መሸሸጊያ ናት—ከሌሎች አማኞች ጋር ኢየሱስን ለመምሰል በመሞከር እግዚአብሔርን የምታመልኩበት ቦታ ነው። መጥተው እንዲጎበኙ እንፈልጋለን!
Pacific, New Zealand, Stock Photos
እምነቶቻችን
ሁሉም እምነቶቻችን እግዚአብሔርን እና ኢየሱስ ክርስቶስን ማእከል ያደረጉ ናቸው። ስለምናምንባቸው ነገሮች እና እነዚያ ዋና መሰረታዊ እምነቶች አዳኙን መከተል እንድትችሉ እንዴት ሊያነሳሳችሁ እንደሚች የበለጠ ተማሩ።
ይወቁን
Pacific, Tonga, Stock Photos
ስለ እኛ በይበልጥ ይወቁ።
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላትን በመላው አለም ያገኛሉ። አለምን የተሻለች ቦታ ለማድረግ አብረን እየሰራን የምንገኝ ጓደኞቻችሁ እና ጎረቤቶቻችሁ ነን።

የቤተክርስቲያንን የቅርብ ጊዜ ዜናዎችን ያግኙ።

በዓለም ዙሪያ መልካም ነገሮች እየተከሰቱ ነው። በቤተክርስቲያኗ ፕሮጀክቶች፣ ዝግጅቶች፣ የአደጋ ጊዜ እርዳታ ጥረቶች እና ሌሎች ላይ ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ።

የዜና ክፍልን ይጎብኙ
Chile: Family Life
በአቅራቢያዎ የሚገኝ ቤተክርስቲያን
ያግኙ
ከሚስዮናዊያን ጋር ይገናኙ
መፅሐፈ ሞርሞንን ያጥኑ